Tuesday, 11 September 2018

ይናገራል ፎቶ: ኢትዮጵያ ትናንት ዛሬና ነገ


በዘመነ ኢሕአዴግ/ወያኔ ኢትዮጵያውያን ብዙ ተግዳሮቶችን ሲጋፈጡ ኖረዋል:: ባለፈው 2010 ዓ/ም ጽዋው ሞልቶ ግፍና መከራ የሚያበቃበት ምዕራፍ በሕዝብ ትግል ተከፍቷል:: /ር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመመረጣቸው በፊትና በኋላ ያለውን ክስተት ሁሉ የሚዘግቡ በርካታ መጽሐፍት ሊዘጋጁ ይችላሉ:: ይሁንና በይፋ የሚታወቁ ክስተቶችን አንስቶ መወያየት ብዙም አያስቸግርም:: ባለፈው ዓመት የተከሰቱና ወደፊትም ሊከሰቱ የሚችሉ ጥቂት አስተሳሰቦችንና ድርጊቶችን በፎቶ ወይም በሥዕል መግለጽ ይቻላል:: ይናገራል ፎቶ ይባል የለ! ለእይታ ይመች ዘንድ ሁለት የጊዜ ወሰኖችን ለይቻለሁ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጡረታ እስከወጡበት ድረስ ያለውን የመንግስት አስተሳሰብና የተፈጸሙትን ግፎች በመጀመሪያ ደረጃ በሥዕል ለማሳየት ሞክሬያለሁ:: ይህንም  ከለውጥ በፊት ብዬ ሰይሜዋለሁ:: ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ኃይለ ማርያም ጡረታ ከወጡበት ጀምሮ ያለውን ሂደት ያመላክታል:: በተለይም ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመመረጣቸው በፊት የነበረውን ጥቂት ጊዜና እስካሁንም ድረስ ያለውን ያካትታል:: ይህንም ከለውጥ በኋላ ብዬ ሰይሜዋለሁ::
  

Wednesday, 1 August 2018

የቅዱስ ሲኖዶስ አንድነት ታወጀ!


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 2ኛው ዙር የሰላምና የአንድነት ጉባኤ 24 አባላት ያሉት ጠቅላላ ጉባኤ 12 አባላት ያሉት ሥራ አሥፈፃሚ አባላትና 6 አባላት ያሉት ጽ/ቤት አዋቅሮ የቅዱስ ሲኖዶስን አንድነት ለማምጣት ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ጥሯል፡፡ ዓላማውን ለማሳካት በሰሜን አሜሪካ፤ በአውሮፓና በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል፡፡ በአሜሪካና በአውሮፓ ያሉ አብያተ ክርስቲያናትና ምእመናን ከፍተኛ ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡ የእግዚአብር ፈቃድ ሆኖ ሁለቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሶች አንድነት እንደመሰረቱ ለ2ኛው ዙር የሰላምና የአንድነት ጉባኤ አባላት ሐምሌ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው ምተን ኢን ሂልተን ሆቴል ተበሰረ፡፡

Friday, 22 June 2018

የሁለቱ ሲኖዶሶች ፈተና


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕወሓት- መሩ መንግስት ከመጣ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመጋፈጥ ላይ ትገኛለች። ኦርቶዶክስንና አማራን በተለየ መልኩ ለማዳከም ከተቻለም ለማጥፋት የትግሉ ዓላማ አድርጎ የተነሳው ቡድን ሥልጣን በያዘ ማግስት ያለምንም ፍርሃትና ይሉኝታ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ገብቶ ማወክ ጀመረ። ባለሥልጣናቱ ኦርቶዶክስነትንና አማራነትን ብሎም ኢትዮጵያዊነትን በመድረክ በሚዲያ መደብደብ በገሃድም ማፈን ጀመሩ።    

Tuesday, 12 June 2018

ዶ/ር ዐቢይና ሥር ነቀል ለውጥ በኢትዮጵያ


/ር ዐቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ አመለካከቶችን በማንጸባረቅ ላይ ይገኛሉ ጠቅለል ባለ ዳሩ ግን ጥናታዊ ባልሆነ መልኩ ሲታይ ዶ/ሩ ከሚናገሯቸውና ከሚያከናውኗቸው ሥራዎች አንጻር ኢትዮጵያውያንን በአመለካከታቸው በአራት ምድብ ማስቀመጥ ይቻላል የመጀመሪያዎቹ  ለውጡን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው የሚወዱ ዶ/ሩንም እንደ መሲህ የሚመለከቱ ናቸው የዶ/ሩን ንግግሮችና ሥራዎች በመዘርዘር ራሳቸውን በአውንታዊ መልኩ አሳምነው ሌሎችንም ለማሳመን ይጥራሉ ከአሁን በኋላ አስተማማኝና ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው በጦር ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ በመታገል እንደሆነ ዐቢይን ተምሳሌት አድርገው ያቀርባሉ በቅርቡ ኢትዮጵያ የገቡ የተቃዋሚ አመራር አባላትን ጨምሮ ቀላል ሊባል የማይችል ሕዝብ በዚህ የአመለካከት ጎራ ሊመደብ ይችላል      

Wednesday, 14 February 2018

ኢትዮጵያ ለዘላለም እንድትኖር!

ኢትዮጵያዊያን እጅግ የተቀናጀ ያመረረና ቀጣይነትም ያለው ተቃውሞ በመንግስት ላይ እያካሄዱ ይገኛሉ። ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሏል።  መሠረታዊ የሆኑ የመብትና የነጻነት እንዲሁም የፍትህ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ይህንም ተከትሎ ቁጥራቸው በግልጽ ያልታወቀ ኢትዮጵያውያኖች በመንግስት ታጣቂዎች ተገለዋል ቆስለዋል ታስረዋል ይህም ሁሉ መከራ ወርዶ ሕዝቡ ለበለጠ ትግል ተነሳስቷል። እስካሁን የተከናወኑት ክስተቶች እንዲሁም ሕዝቡ የሚያስተጋባቸው መፈክሮች በግልጽ እንደሚያሳዩት መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከምን ጊዜውም በላይ ተቀባይነትን አጥቷል። የጉልበት አገዛዝ ጊዜው አልፎበታል። ይህንም መንግስት ራሱ በደንብ የተገነዘበ ይመስላል። የፖለቲካ እስረኞች መፈታትም የዚሁ አካል እንደሆነ መገመት የሚያሻማ አይመስልም። ይሁንና ሕዝባዊ ትግሉ የመጨረሻ ዓላማውን እስኪመታ ድረስ ተቀናጅቶ መቀጠል ይኖርበታል።     

Wednesday, 20 December 2017

Save Ethiopia by Saving the TPLF!

The (civil and armed) struggle against the Tigray People’s Liberation Front (TPLF)-led system in Ethiopia seems unabatable. The notorious Federal Police and even the military cannot so far stop it. Even those in power painfully and publicly acknowledge that something significant and consequential is closing in against them. The regime that strangled the nation for over two decades now seems derailing off track.  

Friday, 11 August 2017

ሕዝባዊ ትግሉና ዲያስፖራው

ሕዝባዊ ትግል ወይም አመጽ ወሳኝ የትግል ስልት መሆን እንደሚችል ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን እያካሄዱት ያሉት ትግል ጥሩ ማስረጃ ነው። ትግሉ እስካሁን ድረስ ከተገመተው በላይ በርካታ ድሎችን አስገኝቷል። ቀጥለው የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ክስተቶች  የትግሉ ውጤት እንደሆኑ መናገር ይቻላል። አንደኛ መንግስት ሊተገብራቸው ያቀዳቸውን ፕሮጀክቶች ለጊዜውም ቢሆን በሕዝብ ትግል የተነሳ እንዲቆሙ አድርጓል። ሁለተኛ ትግሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ አድርጓል። ሦስተኛ የክልል ባለ ሥልጣናት በተወሰነ መልኩ ሕወሓትን እንዲገዳደሩ የሞራል ተነሳሽነት ሰጥቷል።

ይናገራል ፎቶ: ኢትዮጵያ ትናንት ዛሬና ነገ

በዘመነ ኢሕአዴግ / ወያኔ ኢትዮጵያውያን ብዙ ተግዳሮቶችን ሲጋፈጡ ኖረዋል :: ባለፈው 2010 ዓ / ም ጽዋው ሞልቶ ግፍና መከራ የሚያበቃበት ምዕራፍ በሕዝብ ትግል ተከፍቷል :: ዶ / ር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ...