Thursday 8 December 2016

ኢትዮጵያዊ የዐማራ ተጋድሎ

  ከጥቂት ወራት ወዲህ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረ ከሳቡ ወሳኝ ጉዳዮች ውስጥ የዐማራ መደራጀት ዋናው ሳይሆን አልቀረም ይህን ጉዳይ በተመለከተ በርካታ ጽሑፎችና ንግግሮች ተደርገዋል ዐማራው እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነገድ መደራጀትና ራሱን ከተቀነባበረ ጥፋት ማዳን እንዳለበት የሚሞግቱ በርካቶች ናቸው አሳማኝ የመከራከሪያ ነጥቦችንም አንስተዋል በአንጻሩ ደግሞ ዐማራው በኢትዮጵያዊነት እንጅ በነገዱ መታገል መዘዙ ብዙ እንደሆነ ያስጠነቀቁ አሉ ከሁለቱም ወገኖች አንዳንዶች ነጥቦቻቸውን በምክንያት ወይም በመረጃና በማስረጃ መደገፍ ሲሳናቸው አፍ አውጥተው ሌሎች ጸሐፍትን ሲሳደቡና «ወያኔ ነህ» «ጸረ ዐማራ ነህ» እያሉ ሲያሸማቅቁ ታይተዋል ከነዚህ ከተሳዳቢዎችና ከአሸማቃቂዎች በስተቀር ለሌሎች ጸሐፍት ከፍ ያለ አክብሮትና ምሥጋና አቀርባለሁ መሠረት ያላቸው ውይይቶችና ክርክሮች ለሚደረገው ትግል ግልጽነትንና    መናበብን ይፈጥራሉና!      

Who will Win: Fano or the Government?

  The government's war for "disarmament" in the Amhara region has become much more   complicated than everyone’s expectation. ...