ባህል ብዙ ትርጉም ይኖረዋል:: ለእኔ ግን የአንድ ኅብረተሰብ የአስተሳሰብ: የጠባይና: የባህርይ መገለጫ ወይም
ምልክት ነው:: በተፈጥሮ (በዘር ውርስ) የማይገኝና በሰው ብርቱ ጥረት የሚፈጠር ስለሆነ እያንዳንዱ አገር የራሱ የሆነ ልዩ
ባህል አለው:: ለልጅ ልጅም በትምህርትና በተሞክሮ ያስተላልፋል:: በጊዜ ብዛትና በተለያዩ ብሄራዊ: ክልላዊና: ዓለም አቀፋዊ ጫናዎች የተነሳ ባህል ሊከለስ ሊዳብር ሊለወጥም ይችላል:: ያም ቢሆን ግን አገራት በባህላቸው ልዩ የሆኑ ናቸው (የዓለም ህዝቦች የሚጋሩትም ባህል እንዳለ ሳንረሳ):: በአጠቃላይ ባህል የኅብረተሰብን ምንነትንና ማንነትን ገላጭ ነው ቢባል የተጋነነ አይሆንም::