Saturday 16 April 2016

ማኅበረ ቅዱሳንና አራቱ ፈታኞች ክፍል 2

ክፍል 1 ጽሑፌ ስለማኅበረ ቅዱሳን (ማቅ) መጻፍ ለምን እንዳስፈለገ ማኅበሩን እንዴት እንዳወቅኩትና ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የማኅበሩን አመሰራረትና ዓላማ በጥቂቱ አቅርቤያለሁ በዚህ ክፍል ደግሞ ማቅን አብዝተው የሚፈትኑ አካላት እነማን እንደሆኑ በደረጃ ከነምክንያቶቻቸው አቀርባለሁ ይህ ጽሑፍ በክፍል 1 እንደተጠቀሰው ማቅንም ሆነ ሌላ አካልን ለመቃወምም ሆነ ለመደገፍ የተዘጋጀ አይደለም ያሉ እውነታዎችን ከግል እይታዬ በመነሳት በትንተና መልክ ለአንባቢ ማስገንዘብ እንጅበዚህ ጽሑፍ ምክንያት ሊነሱ የሚችሉ ውይይቶችና ሙግቶች በመጨረሻ የተሻለ ግንዛቤ እንዲመጣ ያደርጋሉ ብዬ አምናለሁ። ለጽሑፎቼ እንደ ግብዓት ያገለገሉኝ የግል ተሞክሮዬ የማቅ ገጸ ድርና እትሞች እንዲሁም ስለማቅ በተለያዩ ሚዲያዎች የተነሱ ዘገባዎች ናቸው    

Friday 8 April 2016

ማኅበረ ቅዱሳንና አራቱ ፈታኞች

ማኅበረ ቅዱሳንን በሚገባ ያወቅሁት የዛሬ 20 ዓመት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ግቢ የመጀመሪያ ድግሪ ተማሪ እያለሁ ነው ማኅበሩ ገና በእግሩ ለመቆም ጥረት በሚያደርግበት ወቅት  ማኅበረ ቅዱሳን (ከዚህ በኋላ ለማሳጠር ያህል ማቅ ወይም ማኅበሩ እያልኩ እጽፋለሁ) ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ በዩኒቨርስቲው ዋና ግቢ ያሉትን ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ በሚገኘው ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባቋቋሙት ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ጋበዘ  ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ በሰንበት ትምህርት ቤት ተሳታፊ ስለነበርኩና የዕውቀትም ጥማት ስለነበረብኝ የማኅበሩን ግብዣ በታላቅ ደስታ ተቀበልኩት

Who will Win: Fano or the Government?

  The government's war for "disarmament" in the Amhara region has become much more   complicated than everyone’s expectation. ...