በዚህ የመጨረሻ ክፍል ከአስተሳሰባችንና ከአመለካከታችን ጋር ቀጥታዊ ግንኙነት አለው ብዬ የማስበውን ጎጂ ባህል አቀርባለሁ:: ይህን ጎጂ ባህል በሚገባ መመርመርና ማስወገድ ከቻልን አገራችን ኢትዮጵያ ከምትገኝበት ሁለንታዊ ችግሮችና ቀውሶች ለመላቀቅ የሚያስችላትን ትክክለኛ መንገድ ልትይዝ ትችላለች:: ቀጣይነት አስተማማኝና ሁሉን አቀፍ የሆነ የእድገታዊ ለውጥ መሰረት ሊጣል ይችላል:: ነገር ግን ይህን ጎጂ ባህል ተቋቁሞ ማለፍና ለቀጣይ ብሄራዊ ለውጥ መስራት ፈታኝ እንደሆነ ግልጽ መሆን አለበት:: ይህን ጎጂ ባህል አጠር አድርጌ ከገለጽኩ በኋላ መፍትሄ ጠቋሚ ሃሳቦች ላይ አተኩራለሁ::