የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕወሓት- መሩ መንግስት ከመጣ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመጋፈጥ ላይ ትገኛለች። ኦርቶዶክስንና አማራን በተለየ መልኩ ለማዳከም
ከተቻለም ለማጥፋት የትግሉ ዓላማ አድርጎ የተነሳው ቡድን ሥልጣን በያዘ ማግስት ያለምንም ፍርሃትና ይሉኝታ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ
ገብቶ ማወክ ጀመረ። ባለሥልጣናቱ ኦርቶዶክስነትንና አማራነትን ብሎም ኢትዮጵያዊነትን በመድረክ በሚዲያ መደብደብ በገሃድም ማፈን
ጀመሩ።
Friday, 22 June 2018
Tuesday, 12 June 2018
ዶ/ር ዐቢይና ሥር ነቀል ለውጥ በኢትዮጵያ
ዶ/ር ዐቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ አመለካከቶችን በማንጸባረቅ
ላይ ይገኛሉ። ጠቅለል ባለ ዳሩ ግን ጥናታዊ ባልሆነ
መልኩ ሲታይ ዶ/ሩ ከሚናገሯቸውና ከሚያከናውኗቸው ሥራዎች አንጻር ኢትዮጵያውያንን
በአመለካከታቸው በአራት ምድብ ማስቀመጥ ይቻላል። የመጀመሪያዎቹ ለውጡን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው የሚወዱ ዶ/ሩንም እንደ መሲህ የሚመለከቱ ናቸው። የዶ/ሩን ንግግሮችና ሥራዎች በመዘርዘር ራሳቸውን በአውንታዊ መልኩ አሳምነው ሌሎችንም ለማሳመን
ይጥራሉ። ከአሁን በኋላ አስተማማኝና ዘላቂ
ለውጥ የሚመጣው በጦር ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ በመታገል እንደሆነ ዐቢይን ተምሳሌት አድርገው ያቀርባሉ። በቅርቡ ኢትዮጵያ የገቡ የተቃዋሚ አመራር አባላትን ጨምሮ
ቀላል ሊባል የማይችል ሕዝብ በዚህ የአመለካከት ጎራ ሊመደብ ይችላል።
Subscribe to:
Posts (Atom)
Who will Win: Fano or the Government?
The government's war for "disarmament" in the Amhara region has become much more complicated than everyone’s expectation. ...