Monday 30 August 2021

ሁሉን ነገር ትተን እኛው እንታረቅ!

     ኢትዮጵያ ያለችበትን ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ሊፈታላት የሚችለው ፍቱን መድኃኒት ብሔራዊ መግባባትና እርቅ እንደሆነ የተለያዩ አካላት እየሰበኩ ይገኛሉ። ምዕራባዊ ሀገራትና የተባበሩት መንግስታት በቀጥታና በተዘዋዋሪ እያስተጋቡት ያለው አጀንዳ የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ሳይስብ አልቀረም። በተለይም የቀውሱ ሁሉ ምንጭና ዋና ተዋናይ የሆነው ሕወሓት የብሔራዊ መግባባትና እርቅ ዋና አካል እንዲሆን መወትወታቸው ግርምትን ሳይፈጥር አልቀረም። ሕወሓት በበኩሉ መግባባትና እርቅ እንደሚካሄድ አምኖና እርግጠኛ ሆኖ አደራዳሪ በመምረጥ ላይ የተጠመደ ይመስላል። የኢትዮጵያ ማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃንም ብሔራዊ መግባባትንና እርቅን እንደ ትልቅ አጀንዳ አድርገው ባያራግቡትም የማይናቅ ትኩረት ሰጥተውታል። አንዳንዶች ሕወሓት በብሔራዊ መግባባትና እርቅ መሳተፍ እንደሌለበት ሳይጠቁሙ አላለፉም። 

Who will Win: Fano or the Government?

  The government's war for "disarmament" in the Amhara region has become much more   complicated than everyone’s expectation. ...