Saturday, 26 November 2016

Asrat Woldeyes & Ethiopian Politics

September 1997. I was in Bichena, the stronghold of the hero Belay Zeleke. My plan
was to reach at Addis Ababa University (AAU) for registration as a final year 
undergraduate student. Unfortunately, the scheduled bus failed to appear. Everyday 
around 6pm, we passengers were supposed to get registered afresh, hoping the bus 
could come the next day. We did registration six times, that is for six days. My 
money generously given by my relatives run real fast and I was in shock. But most 
worrisome was whether I could reach for the registration at AAU. Every passing day 
seriously touched my nerves. That time, no mobile, no Internet. It was real dark time.

Saturday, 8 October 2016

የወቅቱ ፖለቲካዊ አሰላለፍና ፋይዳው

የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል እየሰፋና ቀጣይነቱን እያረጋገጠ ሲሄድ በውጭው ዓለም የሚገኙ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ባህርያቸውን ይበልጥ እየገለጡ መጥተዋል። ግለሰብ ተኮር እንቅስቃሴዎች ወደ ድርጅት ወይም ማኀበር ወይም ኅብረት እየተለወጡ ነው። ይበልጥ ትኩረት እየሳበ የመጣው ግን የድርጅቶቹ ብዛት ሳይሆን የተነሱበት ዓላማ ወይም ግብ ነው። የአንዳንዶች የትግል ባህርይ ከተጠበቀው በአንፃሩ ሆኖ በመገኘቱ ጥቂት በማይባሉ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ቁጣና ግርምትን ፈጥሯል። ይህን ተከትሎ ክርክሮችና ተግሳጾች በመገናኛ ብዙኃን እየወጡ ነው። እኒህ አይነት እንቅስቃሴዎች ትግሉ ምን ያህል ሰላማዊና አንድነትን የተላበሰ እንደሚሆን ካሁኑ ግርታን ፈጥረዋል።

Friday, 9 September 2016

ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ!

በአገራችን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ፣ አሳሳቢ፣ አጓጊም ሆኗል። ፈጣሪ በኋላም ዓለም አቀፍና ብሄራዊ ሕግጋት የሰጧቸውን በፍጹም በነጻነት የመኖር መብታቸው እንዲከበርላቸው የጠየቁ ወገኖቻችን በመሰዋታቸው፣ አካለ ስንኩላን በመሆናቸው፣ የሲዖል አምሳያ በሆኑ እስር ቤቶች በመጋዛቸው፣ መከራ ለበዛበት ስደት በመዳረጋቸው፣ ባጠቃላይ እንደ ሰው በሰላም መኖር ባለመቻላቸው ሃዘናችን ወሰን የለውም።  በአንጻሩ ደግሞ ለመኖር እየተደረገ ያለው አለመኖር ማለትም ትግል መንግስትን ክፉኛ ስላሸበረውና ደካማነቱን ከምንም ጊዜ በላይ አጉልቶ በማሳየቱ ሁኔታውን አጓጊ አድርጎታል። ምንም ይሁን ምን ካሁን በኋላ መንግስትም ሕዝብም በነበሩበት የመግዛትና የመገዛት ሂደት ውስጥ መቀጠል አይችሉም። ይህም አንዳች ለውጥ ሊመጣ እንዳለው አመላካች ስለሆነ ትግሉ ውጤታማ እየሆነ እንደመጣ ይገነዘቧል። 


Friday, 19 August 2016

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር!

ታሪካዊ የለውጥ ጎዳና ለኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በአገራችን እየተደረገ ያለው የሕዝብ ተቃውሞ አስፈላጊና አበረታች እንደሆነ ሞግቻለሁ። የትግሉም ዓላማ እውነተኛና ዘላቂ ዴሞክራሲና ነጻነት ማስፈን እንደሆነም ከሕዝቡ መፈክሮች በመነሳት አትቻለሁ። በተጨማሪም መንግስትና ደጋፊዎቹ፣ ትግሉን በማካሄድ ላይ ያለው ሰፊው ሕዝብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማትና የመገናኛ ብዙኅን ይህን መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ልዩና ላቅ ያለ አስተዋጽዖ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁሜያለሁ። ሕዝቡ የትግሉ ባለቤትና ኦዲተር ሆኖ ሥራ አሥፈጻሚ አካል ወይም ልዩ ብሄራዊ ኮሚቴ መምረጥ እንዳለበትም ለማሳየት ሞክሬ ነበር። በመጨረሻም ኮሚቴው ለምንና እንዴት መመረጥ እንዳለበት ለመነሻ ያህል ጥቂት ነጥቦችን አንስቻለሁ። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ይህ ለውጥ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዴት እንደሚመረጥና የትግል መርሆቹና ስልቶቹ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ዘርዘር አድርጌ አቀርባለሁ።    

Wednesday, 10 August 2016

ታሪካዊ የለውጥ ጎዳና ለኢትዮጵያ

ኢትዮጵያዊያን እጅግ የተቀናጀ፣ ያመረረና ቀጣይነትም ያለው የሚመስል ተቃውሞ በመንግስት ላይ እያካሄዱ ይገኛሉ። ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሏል። የአዲስ አበባ የመስፋፋት እቅድና የመሬት ቅርምት እና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ቢያነሳሱትም መሠረታዊ የሆኑ የመብትና የነጻነት እንዲሁም የፍትህ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ትግሉ በሰላማዊ ሰልፍ ተጀምሮ ሁለ ገብ የሆኑ ስልቶችን ወደ መጠቀም የተሸጋገረ ይመስላል። በመቶዎች የሚቆጠሩት ሰልፈኞች በመንግስት ታጣቂዎች ተገለዋል፣ ቆስለዋል፣ ታስረዋል። ከመንግስት በኩልም ቁጥራቸው ያልታወቀ ወገኖች ሞተዋል፣ ቆስለዋል።  የታሰሩ ግን የሉም። ይህም ሁሉ መከራ ወርዶ ህዝቡ ለበለጠ ትግል ተነሳስቷል። እስካሁን የተከናወኑት ክስተቶች እንዲሁም ህዝቡ የሚያስተጋባቸው መፈክሮች በግልጽ እንደሚያሳዩት መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ በህዝቡ ዘንድ  ተቀባይነትን እንዳጣ ለመረዳት ችሏል። ለመሆኑ ህዝባዊ ትግሉ አስፈላጊ ነውን?  

Thursday, 30 June 2016

ማኅበረ ቅዱሳንና ፈታኞቹ የመጨረሻው ክፍል

መግቢያ
ስለወቅታዊ ጉዳዮች ለመጻፍ ተነሳስቼ ነበር። ዳሩ ግን ከዚህ በፊት ስለማኅበረ ቅዱሳን ሁለት ተከታታይ ጽሑፎችን አቅርቤ ሦስተኛውን እንደምቀጥልበት ቃል መግባቴ ትዝ አለኝ። ጥቂት አንባቢዎቼም «እስካሁን የጻፍካቸው ሁለቱ ጽሑፎች መግቢያ ናቸው። ዋናውን አስከትልና እንተያያለን!» ብለውኝ እንደነበርም ትዝ አለኝ። እናም በሥራ ምክንያት አቋርጨው የነበረውን የጀመርኩትን ጨርሼ እጅግ ወቅታዊ ወደሆኑ ጉዳዮች ማተኮር እንዳለብኝ ወስኜ ይህን የመጨረሻውን ክፍል አቀረብኩ። በዚህ አጋጣሚ አስተያየት የሰጣችሁኝን ሁሉ ከልብ እያመሰገንኩ ወደ ክፍል 3 ላምራ!  

Saturday, 16 April 2016

ማኅበረ ቅዱሳንና አራቱ ፈታኞች ክፍል 2

በክፍል 1 ጽሑፌ ስለማኅበረ ቅዱሳን (ማቅ) መጻፍ ለምን እንዳስፈለገ፣ ማኅበሩን እንዴት እንዳወቅኩትና ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የማኅበሩን አመሰራረትና ዓላማ በጥቂቱ አቅርቤያለሁ። በዚህ ክፍል ደግሞ ማቅን አብዝተው የሚፈትኑ አካላት እነማን እንደሆኑ በደረጃ ከነምክንያቶቻቸው አቀርባለሁ። ይህ ጽሑፍ በክፍል 1 እንደተጠቀሰው ማቅንም ሆነ ሌላ አካልን ለመቃወምም ሆነ ለመደገፍ የተዘጋጀ አይደለም። ያሉ እውነታዎችን ከግል እይታዬ በመነሳት በትንተና መልክ ለአንባቢ ማስገንዘብ እንጅ። በዚህ ጽሑፍ ምክንያት ሊነሱ የሚችሉ ውይይቶችና ሙግቶች በመጨረሻ የተሻለ ግንዛቤ እንዲመጣ ያደርጋሉ ብዬ አምናለሁ። ለጽሑፎቼ እንደ ግብዓት ያገለገሉኝ የግል ተሞክሮዬ፣ የማቅ ገጸ ድርና እትሞች እንዲሁም ስለማቅ በተለያዩ ሚዲያዎች የተነሱ ዘገባዎች ናቸው።    

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church: A Crisis of Spiritual Leadership and Accountability

  1. Introduction: Context, Rationale, and Purpose The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (EOTC) is approaching another annual meeting of it...