Saturday, 21 October 2023

የሚያሸንፈው ፋኖ ወይስ መንግስት?

 መንግስት በአማራ ክልል «ትጥቅ ለማስፈታት» የከፈተው ጦርነት ከሚጠብቀውና ከምንጠብቀው በላይ ገዝፎና ተወሳስቦ አግኝቶታል አግኝተነዋል። ጦርነቱ ተፋፍሞ ጎጃምን፣ ጎንደርን፣ ወሎንና ሸዋን በእምብርክክ እያስኬደ ነው። መንግስትም ድሮንን ጨምሮ ከባድ መሣሪያዎችን ሳይቀር ሥራ ላይ ቢያውልም የፋኖን ግስጋሴ መግታት አልቻለም። እንደታሰበው ባጭር ጊዜ ፋኖን ማሸነፍ ቀርቶ ጦርነቱ የመንግስትን ኅልውና ተገዳድሯል፣ የመከላከያን የሞራል ልእልናና ታማኝነትም ክፉኛ ጥያቄ ውስጥ አስገብቶታል። የአማራ ክልላዊ መንግስት ተበትኗል። እንደገና የተዋቀረውም ቢሆን ከባህር ዳር መውጣት የማይችል፣ የመወሰንና የማስፈጸም፣ የመፈጸምም አቅም የሌለው ሁለት ክንፎቹ እንደተሰበሩበት ዳክዬ ግቢ ውስጥ ሲያጠቅስ የሚውል ሆኗል። አዲስ የተሾሙት ፕሬዚዳንትም ቀደም ብሎ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ የነበረውን ያህል ሥልጣን እንኳን የላቸውም። በመሆኑም የአማራ ብልጽግና ከፍተኛ የሞራል ስብራት ብቻ ሳይሆን ኅልውናውም ለመጠበቅ የማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ገብቷል። በሌሎቹ የብልጽግና አቻዎቹ ዓይን ሳይቀር ንቀትና ውርደት ደርሶበታል። በአጠቃላይ ሲታይ የብልጽግና መንግስትና ፓርቲ ኅልውናቸው አደጋ ላይ እንደሆነ በሚገባይ የተገነዘቡ ይመስላሉ። በአሁኑ ጊዜ ትልቁና አንገብጋቢው ጥያቄ ጦርነቱን ማን እንደሚያሸንፍ መገመቱ ላይ ነው። ሁሉቱም አካላት ድሉ የየራሳቸው እንደሆነ ደጋግመው ይናገራሉ። በእርስዎ አተያይ የሚያሸንፈው ፋኖ ነው ወይስ መንግስት? እንዴት?

Who will Win: Fano or the Government?

  The government's war for "disarmament" in the Amhara region has become much more   complicated than everyone’s expectation. ...