Friday, 9 September 2016
Friday, 19 August 2016
ድር ቢያብር አንበሳ ያስር!
ታሪካዊ የለውጥ ጎዳና ለኢትዮጵያ
በሚል ርዕስ በአገራችን እየተደረገ ያለው የሕዝብ ተቃውሞ አስፈላጊና አበረታች እንደሆነ ሞግቻለሁ። የትግሉም ዓላማ እውነተኛና ዘላቂ ዴሞክራሲና ነጻነት ማስፈን እንደሆነም ከሕዝቡ መፈክሮች በመነሳት አትቻለሁ። በተጨማሪም መንግስትና ደጋፊዎቹ፣ ትግሉን በማካሄድ
ላይ ያለው ሰፊው ሕዝብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማትና የመገናኛ ብዙኅን ይህን መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ልዩና ላቅ
ያለ አስተዋጽዖ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁሜያለሁ። ሕዝቡ የትግሉ ባለቤትና ኦዲተር ሆኖ ሥራ አሥፈጻሚ
አካል ወይም ልዩ ብሄራዊ ኮሚቴ መምረጥ እንዳለበትም ለማሳየት ሞክሬ ነበር። በመጨረሻም ኮሚቴው ለምንና
እንዴት መመረጥ እንዳለበት ለመነሻ ያህል ጥቂት ነጥቦችን አንስቻለሁ። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ይህ ለውጥ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዴት እንደሚመረጥና
የትግል መርሆቹና ስልቶቹ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ዘርዘር አድርጌ አቀርባለሁ።
Wednesday, 10 August 2016
ታሪካዊ የለውጥ ጎዳና ለኢትዮጵያ
ኢትዮጵያዊያን እጅግ
የተቀናጀ፣ ያመረረና ቀጣይነትም ያለው የሚመስል ተቃውሞ በመንግስት ላይ እያካሄዱ ይገኛሉ። ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሏል። የአዲስ አበባ የመስፋፋት እቅድና
የመሬት ቅርምት እና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ቢያነሳሱትም መሠረታዊ የሆኑ የመብትና የነጻነት እንዲሁም የፍትህ
ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ትግሉ በሰላማዊ ሰልፍ ተጀምሮ ሁለ ገብ የሆኑ ስልቶችን ወደ መጠቀም የተሸጋገረ ይመስላል። በመቶዎች የሚቆጠሩት
ሰልፈኞች በመንግስት ታጣቂዎች ተገለዋል፣ ቆስለዋል፣ ታስረዋል። ከመንግስት በኩልም ቁጥራቸው ያልታወቀ ወገኖች ሞተዋል፣ ቆስለዋል። የታሰሩ ግን የሉም።
ይህም ሁሉ መከራ ወርዶ ህዝቡ ለበለጠ ትግል ተነሳስቷል። እስካሁን የተከናወኑት ክስተቶች እንዲሁም ህዝቡ የሚያስተጋባቸው መፈክሮች
በግልጽ እንደሚያሳዩት መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን
እንዳጣ ለመረዳት ችሏል። ለመሆኑ ህዝባዊ ትግሉ አስፈላጊ ነውን?
Thursday, 30 June 2016
ማኅበረ ቅዱሳንና ፈታኞቹ የመጨረሻው ክፍል
መግቢያ
ስለወቅታዊ ጉዳዮች ለመጻፍ ተነሳስቼ ነበር። ዳሩ ግን ከዚህ በፊት ስለማኅበረ
ቅዱሳን ሁለት ተከታታይ ጽሑፎችን አቅርቤ ሦስተኛውን እንደምቀጥልበት ቃል መግባቴ ትዝ አለኝ። ጥቂት አንባቢዎቼም «እስካሁን የጻፍካቸው ሁለቱ ጽሑፎች መግቢያ ናቸው። ዋናውን አስከትልና እንተያያለን!» ብለውኝ እንደነበርም ትዝ አለኝ። እናም በሥራ ምክንያት አቋርጨው የነበረውን የጀመርኩትን ጨርሼ እጅግ ወቅታዊ ወደሆኑ ጉዳዮች ማተኮር እንዳለብኝ ወስኜ
ይህን የመጨረሻውን ክፍል አቀረብኩ። በዚህ አጋጣሚ አስተያየት የሰጣችሁኝን ሁሉ ከልብ እያመሰገንኩ ወደ ክፍል 3 ላምራ!
Saturday, 16 April 2016
ማኅበረ ቅዱሳንና አራቱ ፈታኞች ክፍል 2
በክፍል 1 ጽሑፌ ስለማኅበረ ቅዱሳን (ማቅ)
መጻፍ ለምን እንዳስፈለገ፣ ማኅበሩን እንዴት እንዳወቅኩትና ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የማኅበሩን አመሰራረትና ዓላማ
በጥቂቱ አቅርቤያለሁ። በዚህ ክፍል ደግሞ ማቅን አብዝተው የሚፈትኑ አካላት እነማን እንደሆኑ በደረጃ ከነምክንያቶቻቸው
አቀርባለሁ። ይህ ጽሑፍ በክፍል 1 እንደተጠቀሰው ማቅንም ሆነ ሌላ አካልን ለመቃወምም ሆነ ለመደገፍ
የተዘጋጀ አይደለም። ያሉ እውነታዎችን ከግል እይታዬ በመነሳት በትንተና መልክ ለአንባቢ ማስገንዘብ እንጅ። በዚህ ጽሑፍ ምክንያት ሊነሱ የሚችሉ ውይይቶችና
ሙግቶች በመጨረሻ የተሻለ ግንዛቤ እንዲመጣ ያደርጋሉ ብዬ አምናለሁ። ለጽሑፎቼ እንደ ግብዓት ያገለገሉኝ የግል ተሞክሮዬ፣ የማቅ ገጸ ድርና እትሞች እንዲሁም ስለማቅ
በተለያዩ ሚዲያዎች የተነሱ ዘገባዎች ናቸው።
በክፍል 1 ጽሑፌ ስለማኅበረ ቅዱሳን (ማቅ)
መጻፍ ለምን እንዳስፈለገ፣ ማኅበሩን እንዴት እንዳወቅኩትና ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የማኅበሩን አመሰራረትና ዓላማ
በጥቂቱ አቅርቤያለሁ። በዚህ ክፍል ደግሞ ማቅን አብዝተው የሚፈትኑ አካላት እነማን እንደሆኑ በደረጃ ከነምክንያቶቻቸው
አቀርባለሁ። ይህ ጽሑፍ በክፍል 1 እንደተጠቀሰው ማቅንም ሆነ ሌላ አካልን ለመቃወምም ሆነ ለመደገፍ
የተዘጋጀ አይደለም። ያሉ እውነታዎችን ከግል እይታዬ በመነሳት በትንተና መልክ ለአንባቢ ማስገንዘብ እንጅ። በዚህ ጽሑፍ ምክንያት ሊነሱ የሚችሉ ውይይቶችና
ሙግቶች በመጨረሻ የተሻለ ግንዛቤ እንዲመጣ ያደርጋሉ ብዬ አምናለሁ። ለጽሑፎቼ እንደ ግብዓት ያገለገሉኝ የግል ተሞክሮዬ፣ የማቅ ገጸ ድርና እትሞች እንዲሁም ስለማቅ
በተለያዩ ሚዲያዎች የተነሱ ዘገባዎች ናቸው።
Friday, 8 April 2016
ማኅበረ ቅዱሳንና አራቱ ፈታኞች
ማኅበረ ቅዱሳንን በሚገባ ያወቅሁት የዛሬ 20 ዓመት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ግቢ የመጀመሪያ ድግሪ ተማሪ እያለሁ ነው። ማኅበሩ ገና በእግሩ ለመቆም ጥረት በሚያደርግበት ወቅት ። ማኅበረ ቅዱሳን (ከዚህ በኋላ ለማሳጠር ያህል ማቅ ወይም ማኅበሩ እያልኩ እጽፋለሁ) ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ በዩኒቨርስቲው ዋና ግቢ ያሉትን ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ በሚገኘው ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባቋቋሙት ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ጋበዘ ። ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ በሰንበት ትምህርት ቤት ተሳታፊ ስለነበርኩና የዕውቀትም ጥማት ስለነበረብኝ የማኅበሩን ግብዣ በታላቅ ደስታ ተቀበልኩት።
Friday, 5 February 2016
ስደት ክርስትናና ኢትዮጵያዊነት ክፍል 2
ለተገፉት መቆም
ክርስትና በግል የሚኖሩት ሕይወት አይደለም:: «እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት ለባልንጀራው እንጅ»
(ፊል 2: 4) እንዳለ ለሰው ልጅ ሁሉ ይልቁንስ ለኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ደኅንነት ማሰብና የምንችለውን
ማድረግ መንፈሳዊ ግዴታችን ነው:: በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአፍሪካና በአውሮፓም ሳይቀር
ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በመከራ ላይ ናቸው:: የሰው ልጅ የገጠመው ከባድ የተባለ መከራ ሁሉ የደረሰባቸው
አሉ:: በየእስር ቤቶች የሚጉላሉና ጠያቂ ያጡ ብዙዎች ናቸው:: በደላሎችና በአሸባሪዎች እጅ የወደቁት ብዙ ናቸው:: የሰውነት ክፍሎቻቸው ለሽያጭ የቀረቡባቸው አሉ:: በሃይማኖታቸው ምክንያት መስዋዕትነትን የተቀበሉም አሉ:: ባጠቃላይ በሞትና በህይወት መካከል የሚገኙ ወገኖቻችን ብዙዎች ናቸው:: በአገራችን በኢትዮጵያም ቢሆን ያለአግባብ በእስር የሚማቅቁ፣ የሚገደሉ፣ የሚሳደዱ አሉ:: በረሃብ የሚሰቃየው ወገናችንም በሚሊዮን የሚቆጠር ሆኗል:: ሙስናና ዘረኝነት ህዝባችንን ተፈታትኗል:: ለእነዚህ ሁሉ ወገኖች ኢትዮጵያዊያን ሊደርሱላቸው ይገባል:: በጸሎት ከማሳሰብ ጀምሮ ገንዘብና አስፈላጊ ቁሳቁስ በመላክ እንታደጋቸው::
Subscribe to:
Comments (Atom)
The Addis Paradox and Ethiopia’s Zombie State
Why can a state that appears stable in its capital simultaneously be losing governing capacity across much of its territory? This questi...