ኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ልትቀበል አምስት ቀናት ይቀራታል:: 2006 ዓ.ም.:: በዚህ አዲስ ዓመት ሃገራችን ቢያንስ
ዳጎስ ያለ ለውጥ ማየት ይኖርባታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ:: ይህ ደግሞ ምትሃትን ወይም ተአምርን
አይፈልግም:: እያንዳንዳችን ድርሻችንን በሚገባ ከተወጣን ሊሳካ የሚችል ግብ ነው:: ከዚህ አኳያ በኔ እምነት ቀጥለው የተዘረዘሩትን ብንወጣ
በአዲሱ ዓመት ቢያንስ ትክክለኛውን የለውጥ ጎዳና እንይዛለን:: ይህ ታላቅ ሃገራዊ ጎዳና የሚጀምረው ከእያንዳንዳችን ቤትና ግቢ ነው:: ይህ እውነታ ተዘንግቶ ለውጥ ለማምጣት መሞከር የራስን ግቢ ሳያጸዱ ያካባቢን ንጽህና እጠብቃለሁ
ብሎ እንደማሰብ ነው::
ለማናኛውም ቀጥለው የተዘረዘሩትን ብንፈጽም ለውጥ የማይመጣበት ምክንያት የለም::
ለማናኛውም ቀጥለው የተዘረዘሩትን ብንፈጽም ለውጥ የማይመጣበት ምክንያት የለም::
Pic taken from ethiopiaforums.com
- እያንዳንዳችን በፍጹም ነጻነት እንደተፈጠርን መገንዘብና እለት እለት ከማንኛውም አሉታዊ ተጽእኖ ራሳችንን መጠበቅ
- የማንንም ነጻነት ላለመንካት መጠንቀቅ
- በማንኛውም ሁኔታ ያላግባብ የተገፋ የተበደለ ካለ ስለሱ መጮህ መመስከር
- ምንም ይሁን ምን እውነትን መናገርና ሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ ማበረታታት
- የተሳሳቱ ካሉ በጥበብ ስተታቸውን ቁልጭ አርጎ መናገር
- የሚያድግ ድርጅት ነው የሚያድግ ፓርቲ ነው እያሉ ስተት ሲሰራ ዝም ብሎ አለማየት
- ዘርን መሰረት ያደረገ ማህበር ፓርቲ ከመመስረት መቆጠብ
- እኔ ፖለቲካ አያገባኝም አልችልምም ከሚል ገዳይ ቫይረስ ራስን መጠበቅ
- በሰዎች ወይም በድርጅቶች ወይም በፓርቲዎች ድካምና ውድቀት ከመሳለቅ ችግሮች እንዲፈቱ የሚቻለውን ማድረግ
- ለዘለቄታዊ ሰላምና እድገት ሲባል ፖለቲካዊ ትግላችን ጨቋኞችን ሳይቀር አርነት የሚያወጣ መሆን አለበት
- ሰውን በጻፈው እንጅ በግል ህይዎቱ ባደረገው አንተቸው
- ጽሁፎቻችን መፍትሄ ተኮር ቢሆኑ የተወደደና ተፈላጊ ነው
- ማህበራዊ ድር ገጾች ፎቶ ለመለጠፍ ብቻ ሳይሆን ስለሃገራችን ጉዳዮችም የምንወያይባቸው መድረኮች ይሁኑ
- አሰቃቂ ከሆነ ስግብግብነት እራሳችንን እንጠብቅ
- ለዘላቂ ሰላምና ለእውነተኛ ለውጥ የሚታትሩ ሰዎችን ድርጅቶችን በተቻለ ሁሉ እናበረታታ
- ሁሉን አቀፍ የኢትዮጵያውያን ህብረቶችን በውጭ ሃገራት እንመስርት
- ሁሉን አቀፍ ውይይትና ክርክር ከዚያም መግባባትና እርቅ እንዲመጣ እንጣር
መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልዎ!
No comments:
Post a Comment