በዘመነ ኢሕአዴግ/ወያኔ ኢትዮጵያውያን ብዙ ተግዳሮቶችን ሲጋፈጡ ኖረዋል:: ባለፈው 2010 ዓ/ም ጽዋው ሞልቶ ግፍና መከራ የሚያበቃበት ምዕራፍ በሕዝብ ትግል ተከፍቷል:: ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመመረጣቸው በፊትና በኋላ ያለውን ክስተት
ሁሉ የሚዘግቡ በርካታ መጽሐፍት ሊዘጋጁ ይችላሉ:: ይሁንና በይፋ የሚታወቁ ክስተቶችን አንስቶ መወያየት ብዙም አያስቸግርም:: ባለፈው ዓመት የተከሰቱና ወደፊትም ሊከሰቱ የሚችሉ ጥቂት አስተሳሰቦችንና ድርጊቶችን በፎቶ ወይም በሥዕል መግለጽ
ይቻላል:: ይናገራል ፎቶ ይባል የለ! ለእይታ ይመች ዘንድ ሁለት የጊዜ ወሰኖችን ለይቻለሁ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጡረታ እስከወጡበት ድረስ ያለውን የመንግስት አስተሳሰብና የተፈጸሙትን ግፎች በመጀመሪያ
ደረጃ በሥዕል ለማሳየት ሞክሬያለሁ:: ይህንም ከለውጥ በፊት ብዬ ሰይሜዋለሁ:: ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ኃይለ ማርያም ጡረታ ከወጡበት ጀምሮ ያለውን
ሂደት ያመላክታል:: በተለይም ዶ/ር ዐቢይ
አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመመረጣቸው በፊት የነበረውን ጥቂት ጊዜና እስካሁንም ድረስ ያለውን ያካትታል:: ይህንም ከለውጥ በኋላ ብዬ ሰይሜዋለሁ::