በዘመነ ኢሕአዴግ/ወያኔ ኢትዮጵያውያን ብዙ ተግዳሮቶችን ሲጋፈጡ ኖረዋል:: ባለፈው 2010 ዓ/ም ጽዋው ሞልቶ ግፍና መከራ የሚያበቃበት ምዕራፍ በሕዝብ ትግል ተከፍቷል:: ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመመረጣቸው በፊትና በኋላ ያለውን ክስተት
ሁሉ የሚዘግቡ በርካታ መጽሐፍት ሊዘጋጁ ይችላሉ:: ይሁንና በይፋ የሚታወቁ ክስተቶችን አንስቶ መወያየት ብዙም አያስቸግርም:: ባለፈው ዓመት የተከሰቱና ወደፊትም ሊከሰቱ የሚችሉ ጥቂት አስተሳሰቦችንና ድርጊቶችን በፎቶ ወይም በሥዕል መግለጽ
ይቻላል:: ይናገራል ፎቶ ይባል የለ! ለእይታ ይመች ዘንድ ሁለት የጊዜ ወሰኖችን ለይቻለሁ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጡረታ እስከወጡበት ድረስ ያለውን የመንግስት አስተሳሰብና የተፈጸሙትን ግፎች በመጀመሪያ
ደረጃ በሥዕል ለማሳየት ሞክሬያለሁ:: ይህንም ከለውጥ በፊት ብዬ ሰይሜዋለሁ:: ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ኃይለ ማርያም ጡረታ ከወጡበት ጀምሮ ያለውን
ሂደት ያመላክታል:: በተለይም ዶ/ር ዐቢይ
አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመመረጣቸው በፊት የነበረውን ጥቂት ጊዜና እስካሁንም ድረስ ያለውን ያካትታል:: ይህንም ከለውጥ በኋላ ብዬ ሰይሜዋለሁ::
ባጠቃላይ ሲታይ የቀረቡት ሥዕላት የመንግስትን ማንነትና ምንነት በተወሰነ ደረጃ ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ:: ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ሥዕላቱን በተመለከተ ጥቂት ነገሮችን ግን ልበል::
§ ሥዕላቱን የወሰድኳቸው ከድረ ገፆች በተለይም ከፌስቡክ ወዳጆቼ ገፆች ነው:: ለዚህም ምስጋና አቀርባለሁ!
§ ሥዕላቱ ጥልቅ የሆኑ ሀሳቦችን ያስተላልፋሉ:: በደንብ ካየናቸውም ፍልስፍናዎችም ናቸው
§ የቀረቡት ሥዕላት የመንግስትን ሙሉ ማንነትና ምንነት አያመላክቱም:: በጥቂቱ ብቻ ጨልፈው ጉዳዮችን
በቀላሉ እንድናያቸው እንድንረዳ ያግዛሉ
§ አንዳንዶቹ ሥዕላት በተወሰኑ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተፈጸሙ ግፎችን ቢያመላክቱም በሌሎች አካባቢዎች አለመፈጸማቸውን አያመለክቱም
§ ሁሉም ሥዕላት የተዘጋጁት ያለፈውን ግፍና መከራ እያሰብን እንድንብሰለሰል ሳይሆን የሆነብንን እንድናስታውስና ከሱም ለመማር ነው:: ለትውልድም ለማስተላለፍ ነው
§ ይሁንና
አንዳንድ ሥዕላት ለተለያዩ ትርጓሜዎች ሊጋብዙ ይችላሉ:: እርስዎም ሀገራችን ከነበረችበትና ካለችበት ሁኔታ በመነሳት
የራስዎን ትርጉም ይያዙ!
ከለውጡ በፊት
ከለውጡ በኋላ
መልካም አዲስ ዘመን ይሁንልዎ!
No comments:
Post a Comment