ከጥቂት ወራት ወዲህ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረ ከሳቡ ወሳኝ ጉዳዮች ውስጥ የዐማራ
መደራጀት ዋናው ሳይሆን አልቀረም። ይህን ጉዳይ በተመለከተ በርካታ ጽሑፎችና ንግግሮች ተደርገዋል። ዐማራው እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነገድ መደራጀትና ራሱን ከተቀነባበረ ጥፋት
ማዳን እንዳለበት የሚሞግቱ በርካቶች ናቸው። አሳማኝ የመከራከሪያ ነጥቦችንም አንስተዋል። በአንጻሩ ደግሞ ዐማራው በኢትዮጵያዊነት እንጅ በነገዱ መታገል መዘዙ ብዙ እንደሆነ ያስጠነቀቁ አሉ። ከሁለቱም ወገኖች አንዳንዶች ነጥቦቻቸውን በምክንያት ወይም በመረጃና በማስረጃ
መደገፍ ሲሳናቸው አፍ አውጥተው ሌሎች ጸሐፍትን ሲሳደቡና «ወያኔ ነህ» «ጸረ ዐማራ ነህ» እያሉ ሲያሸማቅቁ ታይተዋል። ከነዚህ ከተሳዳቢዎችና ከአሸማቃቂዎች በስተቀር ለሌሎች ጸሐፍት ከፍ ያለ አክብሮትና
ምሥጋና አቀርባለሁ። መሠረት ያላቸው ውይይቶችና ክርክሮች ለሚደረገው ትግል ግልጽነትንና መናበብን ይፈጥራሉና!
Thursday, 8 December 2016
Saturday, 26 November 2016
Asrat Woldeyes & Ethiopian Politics
September 1997. I was in Bichena, the stronghold of the hero Belay Zeleke. My plan
was to reach at Addis Ababa University (AAU) for registration as a final year
undergraduate student. Unfortunately, the scheduled bus failed to appear. Everyday
around 6pm, we passengers were supposed to get registered afresh, hoping the bus
could come the next day. We did registration six times, that is for six days. My
money generously given by my relatives run real fast and I was in shock. But most
worrisome was whether I could reach for the registration at AAU. Every passing day
seriously touched my nerves. That time, no mobile, no Internet. It was real dark time.
undergraduate student. Unfortunately, the scheduled bus failed to appear. Everyday
around 6pm, we passengers were supposed to get registered afresh, hoping the bus
could come the next day. We did registration six times, that is for six days. My
money generously given by my relatives run real fast and I was in shock. But most
worrisome was whether I could reach for the registration at AAU. Every passing day
seriously touched my nerves. That time, no mobile, no Internet. It was real dark time.
Saturday, 8 October 2016
የወቅቱ ፖለቲካዊ አሰላለፍና ፋይዳው
የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል እየሰፋና ቀጣይነቱን እያረጋገጠ ሲሄድ በውጭው ዓለም የሚገኙ
ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ባህርያቸውን ይበልጥ እየገለጡ መጥተዋል። ግለሰብ ተኮር እንቅስቃሴዎች ወደ ድርጅት ወይም ማኀበር ወይም ኅብረት እየተለወጡ
ነው። ይበልጥ ትኩረት እየሳበ
የመጣው ግን የድርጅቶቹ ብዛት ሳይሆን የተነሱበት ዓላማ ወይም ግብ ነው። የአንዳንዶች የትግል ባህርይ ከተጠበቀው በአንፃሩ ሆኖ በመገኘቱ ጥቂት በማይባሉ
ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ቁጣና ግርምትን ፈጥሯል። ይህን ተከትሎ ክርክሮችና ተግሳጾች በመገናኛ ብዙኃን እየወጡ ነው። እኒህ አይነት እንቅስቃሴዎች ትግሉ ምን ያህል ሰላማዊና አንድነትን የተላበሰ እንደሚሆን
ካሁኑ ግርታን ፈጥረዋል።
Friday, 9 September 2016
ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ!
በአገራችን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ፣ አሳሳቢ፣ አጓጊም ሆኗል። ፈጣሪ በኋላም ዓለም አቀፍና ብሄራዊ ሕግጋት የሰጧቸውን በፍጹም በነጻነት የመኖር መብታቸው እንዲከበርላቸው የጠየቁ ወገኖቻችን በመሰዋታቸው፣ አካለ ስንኩላን በመሆናቸው፣ የሲዖል አምሳያ በሆኑ እስር ቤቶች በመጋዛቸው፣ መከራ ለበዛበት ስደት በመዳረጋቸው፣ ባጠቃላይ እንደ ሰው በሰላም መኖር ባለመቻላቸው ሃዘናችን ወሰን የለውም። በአንጻሩ ደግሞ ለመኖር እየተደረገ ያለው አለመኖር ማለትም ትግል መንግስትን ክፉኛ ስላሸበረውና ደካማነቱን ከምንም ጊዜ በላይ አጉልቶ በማሳየቱ ሁኔታውን አጓጊ አድርጎታል። ምንም ይሁን ምን ካሁን በኋላ መንግስትም ሕዝብም በነበሩበት የመግዛትና የመገዛት ሂደት ውስጥ መቀጠል አይችሉም። ይህም አንዳች ለውጥ ሊመጣ እንዳለው አመላካች ስለሆነ ትግሉ ውጤታማ እየሆነ እንደመጣ ይገነዘቧል።
Friday, 19 August 2016
ድር ቢያብር አንበሳ ያስር!
ታሪካዊ የለውጥ ጎዳና ለኢትዮጵያ
በሚል ርዕስ በአገራችን እየተደረገ ያለው የሕዝብ ተቃውሞ አስፈላጊና አበረታች እንደሆነ ሞግቻለሁ። የትግሉም ዓላማ እውነተኛና ዘላቂ ዴሞክራሲና ነጻነት ማስፈን እንደሆነም ከሕዝቡ መፈክሮች በመነሳት አትቻለሁ። በተጨማሪም መንግስትና ደጋፊዎቹ፣ ትግሉን በማካሄድ
ላይ ያለው ሰፊው ሕዝብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማትና የመገናኛ ብዙኅን ይህን መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ልዩና ላቅ
ያለ አስተዋጽዖ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁሜያለሁ። ሕዝቡ የትግሉ ባለቤትና ኦዲተር ሆኖ ሥራ አሥፈጻሚ
አካል ወይም ልዩ ብሄራዊ ኮሚቴ መምረጥ እንዳለበትም ለማሳየት ሞክሬ ነበር። በመጨረሻም ኮሚቴው ለምንና
እንዴት መመረጥ እንዳለበት ለመነሻ ያህል ጥቂት ነጥቦችን አንስቻለሁ። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ይህ ለውጥ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዴት እንደሚመረጥና
የትግል መርሆቹና ስልቶቹ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ዘርዘር አድርጌ አቀርባለሁ።
Wednesday, 10 August 2016
ታሪካዊ የለውጥ ጎዳና ለኢትዮጵያ
ኢትዮጵያዊያን እጅግ
የተቀናጀ፣ ያመረረና ቀጣይነትም ያለው የሚመስል ተቃውሞ በመንግስት ላይ እያካሄዱ ይገኛሉ። ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሏል። የአዲስ አበባ የመስፋፋት እቅድና
የመሬት ቅርምት እና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ቢያነሳሱትም መሠረታዊ የሆኑ የመብትና የነጻነት እንዲሁም የፍትህ
ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ትግሉ በሰላማዊ ሰልፍ ተጀምሮ ሁለ ገብ የሆኑ ስልቶችን ወደ መጠቀም የተሸጋገረ ይመስላል። በመቶዎች የሚቆጠሩት
ሰልፈኞች በመንግስት ታጣቂዎች ተገለዋል፣ ቆስለዋል፣ ታስረዋል። ከመንግስት በኩልም ቁጥራቸው ያልታወቀ ወገኖች ሞተዋል፣ ቆስለዋል። የታሰሩ ግን የሉም።
ይህም ሁሉ መከራ ወርዶ ህዝቡ ለበለጠ ትግል ተነሳስቷል። እስካሁን የተከናወኑት ክስተቶች እንዲሁም ህዝቡ የሚያስተጋባቸው መፈክሮች
በግልጽ እንደሚያሳዩት መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን
እንዳጣ ለመረዳት ችሏል። ለመሆኑ ህዝባዊ ትግሉ አስፈላጊ ነውን?
Thursday, 30 June 2016
ማኅበረ ቅዱሳንና ፈታኞቹ የመጨረሻው ክፍል
መግቢያ
ስለወቅታዊ ጉዳዮች ለመጻፍ ተነሳስቼ ነበር። ዳሩ ግን ከዚህ በፊት ስለማኅበረ
ቅዱሳን ሁለት ተከታታይ ጽሑፎችን አቅርቤ ሦስተኛውን እንደምቀጥልበት ቃል መግባቴ ትዝ አለኝ። ጥቂት አንባቢዎቼም «እስካሁን የጻፍካቸው ሁለቱ ጽሑፎች መግቢያ ናቸው። ዋናውን አስከትልና እንተያያለን!» ብለውኝ እንደነበርም ትዝ አለኝ። እናም በሥራ ምክንያት አቋርጨው የነበረውን የጀመርኩትን ጨርሼ እጅግ ወቅታዊ ወደሆኑ ጉዳዮች ማተኮር እንዳለብኝ ወስኜ
ይህን የመጨረሻውን ክፍል አቀረብኩ። በዚህ አጋጣሚ አስተያየት የሰጣችሁኝን ሁሉ ከልብ እያመሰገንኩ ወደ ክፍል 3 ላምራ!
Subscribe to:
Comments (Atom)
The Addis Paradox and Ethiopia’s Zombie State
Why can a state that appears stable in its capital simultaneously be losing governing capacity across much of its territory? This questi...