የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 2ኛው ዙር የሰላምና
የአንድነት ጉባኤ 24 አባላት ያሉት ጠቅላላ ጉባኤ፤ 12 አባላት ያሉት ሥራ አሥፈፃሚ አባላትና 6 አባላት ያሉት ጽ/ቤት
አዋቅሮ የቅዱስ ሲኖዶስን አንድነት ለማምጣት ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ጥሯል፡፡ ዓላማውን ለማሳካት በሰሜን አሜሪካ፤ በአውሮፓና በኢትዮጵያ
ቅርንጫፍ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል፡፡ በአሜሪካና በአውሮፓ ያሉ አብያተ ክርስቲያናትና ምእመናን ከፍተኛ ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ሁለቱ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሶች አንድነት እንደመሰረቱ ለ2ኛው ዙር የሰላምና የአንድነት ጉባኤ አባላት
ሐምሌ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው ሀምተን ኢን ሂልተን ሆቴል ተበሰረ፡፡
Wednesday, 1 August 2018
Friday, 22 June 2018
የሁለቱ ሲኖዶሶች ፈተና
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕወሓት- መሩ መንግስት ከመጣ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመጋፈጥ ላይ ትገኛለች። ኦርቶዶክስንና አማራን በተለየ መልኩ ለማዳከም
ከተቻለም ለማጥፋት የትግሉ ዓላማ አድርጎ የተነሳው ቡድን ሥልጣን በያዘ ማግስት ያለምንም ፍርሃትና ይሉኝታ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ
ገብቶ ማወክ ጀመረ። ባለሥልጣናቱ ኦርቶዶክስነትንና አማራነትን ብሎም ኢትዮጵያዊነትን በመድረክ በሚዲያ መደብደብ በገሃድም ማፈን
ጀመሩ።
Tuesday, 12 June 2018
ዶ/ር ዐቢይና ሥር ነቀል ለውጥ በኢትዮጵያ
ዶ/ር ዐቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ አመለካከቶችን በማንጸባረቅ
ላይ ይገኛሉ። ጠቅለል ባለ ዳሩ ግን ጥናታዊ ባልሆነ
መልኩ ሲታይ ዶ/ሩ ከሚናገሯቸውና ከሚያከናውኗቸው ሥራዎች አንጻር ኢትዮጵያውያንን
በአመለካከታቸው በአራት ምድብ ማስቀመጥ ይቻላል። የመጀመሪያዎቹ ለውጡን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው የሚወዱ ዶ/ሩንም እንደ መሲህ የሚመለከቱ ናቸው። የዶ/ሩን ንግግሮችና ሥራዎች በመዘርዘር ራሳቸውን በአውንታዊ መልኩ አሳምነው ሌሎችንም ለማሳመን
ይጥራሉ። ከአሁን በኋላ አስተማማኝና ዘላቂ
ለውጥ የሚመጣው በጦር ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ በመታገል እንደሆነ ዐቢይን ተምሳሌት አድርገው ያቀርባሉ። በቅርቡ ኢትዮጵያ የገቡ የተቃዋሚ አመራር አባላትን ጨምሮ
ቀላል ሊባል የማይችል ሕዝብ በዚህ የአመለካከት ጎራ ሊመደብ ይችላል።
Wednesday, 14 February 2018
ኢትዮጵያ ለዘላለም እንድትኖር!
ኢትዮጵያዊያን እጅግ
የተቀናጀ፣ ያመረረና ቀጣይነትም ያለው ተቃውሞ በመንግስት ላይ እያካሄዱ ይገኛሉ። ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሏል። መሠረታዊ የሆኑ የመብትና የነጻነት እንዲሁም የፍትህ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው።
ይህንም ተከትሎ ቁጥራቸው በግልጽ ያልታወቀ ኢትዮጵያውያኖች በመንግስት ታጣቂዎች ተገለዋል፣ ቆስለዋል፣ ታስረዋል። ይህም ሁሉ መከራ ወርዶ ሕዝቡ ለበለጠ
ትግል ተነሳስቷል። እስካሁን የተከናወኑት ክስተቶች እንዲሁም ሕዝቡ የሚያስተጋባቸው መፈክሮች በግልጽ እንደሚያሳዩት መንግስት በከፍተኛ
ሁኔታ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከምን ጊዜውም በላይ ተቀባይነትን አጥቷል። የጉልበት አገዛዝ ጊዜው አልፎበታል። ይህንም መንግስት ራሱ
በደንብ የተገነዘበ ይመስላል። የፖለቲካ እስረኞች መፈታትም የዚሁ አካል እንደሆነ መገመት የሚያሻማ አይመስልም። ይሁንና ሕዝባዊ
ትግሉ የመጨረሻ ዓላማውን እስኪመታ ድረስ ተቀናጅቶ መቀጠል ይኖርበታል።
Wednesday, 20 December 2017
Save Ethiopia by Saving the TPLF!
The (civil and armed) struggle against
the Tigray People’s Liberation Front (TPLF)-led system in Ethiopia seems
unabatable. The notorious Federal Police and even the military cannot so far
stop it. Even those in power painfully and publicly acknowledge that something
significant and consequential is closing in against them. The regime that
strangled the nation for over two decades now seems derailing off track.
Friday, 11 August 2017
ሕዝባዊ ትግሉና ዲያስፖራው
ሕዝባዊ ትግል ወይም አመጽ
ወሳኝ የትግል ስልት መሆን እንደሚችል ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን እያካሄዱት ያሉት ትግል ጥሩ ማስረጃ ነው። ትግሉ
እስካሁን ድረስ ከተገመተው በላይ በርካታ ድሎችን አስገኝቷል። ቀጥለው የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ክስተቶች የትግሉ ውጤት እንደሆኑ መናገር ይቻላል። አንደኛ መንግስት ሊተገብራቸው ያቀዳቸውን
ፕሮጀክቶች ለጊዜውም ቢሆን በሕዝብ ትግል የተነሳ እንዲቆሙ አድርጓል። ሁለተኛ ትግሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ አድርጓል።
ሦስተኛ የክልል ባለ ሥልጣናት በተወሰነ መልኩ ሕወሓትን እንዲገዳደሩ የሞራል ተነሳሽነት ሰጥቷል።
Thursday, 8 December 2016
ኢትዮጵያዊ የዐማራ ተጋድሎ
ከጥቂት ወራት ወዲህ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረ ከሳቡ ወሳኝ ጉዳዮች ውስጥ የዐማራ
መደራጀት ዋናው ሳይሆን አልቀረም። ይህን ጉዳይ በተመለከተ በርካታ ጽሑፎችና ንግግሮች ተደርገዋል። ዐማራው እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነገድ መደራጀትና ራሱን ከተቀነባበረ ጥፋት
ማዳን እንዳለበት የሚሞግቱ በርካቶች ናቸው። አሳማኝ የመከራከሪያ ነጥቦችንም አንስተዋል። በአንጻሩ ደግሞ ዐማራው በኢትዮጵያዊነት እንጅ በነገዱ መታገል መዘዙ ብዙ እንደሆነ ያስጠነቀቁ አሉ። ከሁለቱም ወገኖች አንዳንዶች ነጥቦቻቸውን በምክንያት ወይም በመረጃና በማስረጃ
መደገፍ ሲሳናቸው አፍ አውጥተው ሌሎች ጸሐፍትን ሲሳደቡና «ወያኔ ነህ» «ጸረ ዐማራ ነህ» እያሉ ሲያሸማቅቁ ታይተዋል። ከነዚህ ከተሳዳቢዎችና ከአሸማቃቂዎች በስተቀር ለሌሎች ጸሐፍት ከፍ ያለ አክብሮትና
ምሥጋና አቀርባለሁ። መሠረት ያላቸው ውይይቶችና ክርክሮች ለሚደረገው ትግል ግልጽነትንና መናበብን ይፈጥራሉና!
Subscribe to:
Posts (Atom)
The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church: A Crisis of Spiritual Leadership and Accountability
1. Introduction: Context, Rationale, and Purpose The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (EOTC) is approaching another annual meeting of it...