ሰሞኑን ቅስም ሰባሪ በሆነ ክስተት ውስጥ ራሳችንን አግኝተናል:: ውድ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ ዘግናኝ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተካሄደባቸው ነው:: የችግሮቹን አይነትና መጠን የኢትዮጵያውያን የመገናኛ ብዙኃን በሚገባ እየዘገቡት ነው:: በአጠቃላይ ሲታይ ግን የሳውዲዎችን ርምጃ እንደሰው ለመረዳት የሚከብድ ነው:: በዚህ ዘመንና መንግስት ባለበት አገር እንዴት የሰው ልጅ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ካገር እንዲወጣ ይታሰባል? ህግን ለመጠበቅ ወይም ለማስከበር ሲባል በምንም ዋጋ የማይገኘውን ውድ የሰው ልጅ ህይወትን ማጥፋትና ማጎሳቆል እንዴት ሚዛን
ይደፋል?
Friday, 15 November 2013
Sunday, 20 October 2013
ጎጂ ባህሎቻችን
ባህል ብዙ ትርጉም ይኖረዋል:: ለእኔ ግን የአንድ ኅብረተሰብ የአስተሳሰብ: የጠባይና: የባህርይ መገለጫ ወይም
ምልክት ነው:: በተፈጥሮ (በዘር ውርስ) የማይገኝና በሰው ብርቱ ጥረት የሚፈጠር ስለሆነ እያንዳንዱ አገር የራሱ የሆነ ልዩ
ባህል አለው:: ለልጅ ልጅም በትምህርትና በተሞክሮ ያስተላልፋል:: በጊዜ ብዛትና በተለያዩ ብሄራዊ: ክልላዊና: ዓለም አቀፋዊ ጫናዎች የተነሳ ባህል ሊከለስ ሊዳብር ሊለወጥም ይችላል:: ያም ቢሆን ግን አገራት በባህላቸው ልዩ የሆኑ ናቸው (የዓለም ህዝቦች የሚጋሩትም ባህል እንዳለ ሳንረሳ):: በአጠቃላይ ባህል የኅብረተሰብን ምንነትንና ማንነትን ገላጭ ነው ቢባል የተጋነነ አይሆንም::
Thursday, 26 September 2013
የማታ እንጀራ ይስጥህ!
አገር ቤት ያደገ ወይም የቆየ ሰው ብዙ አባባሎችንና ምርቃኖችን እድሜ ከጠገቡ (እድሜ ካስቆጠሩ) ሰዎች ይሰማል ይማራል:: ከነዚህም ውስጥ የማታ እንጀራ ይስጥህ የሚለው ምርቃት ቀልብን ይስባል:: ገና ነፍስ ሳላውቅ የዚህ አባባል ትርጉም አይገባኝም ነበር:: ትርጉሙን የመጠየቅም እድሉና አቅሙ አልነበረኝም:: ነገር ግን በ20ዎቹ የእድሜየ ክልል ሳለሁ አንድ የተባረከ ሰው ትርጉሙን ሲያብራራ ሰማሁት:: ሳልጠይቅ ያገኘሁት መልስ ነበር:: ከዚያ በኋላ ለአባባሉ ልዩ ክብር መስጠት ጀመርኩ::
Friday, 13 September 2013
አዲስ ፕሬዚደንት በአዲስ ዓመት
ሰባት ዓመት ገደማ ነው:: ባህር ዳር ከተማ ፓፒረስ ሆቴል ሻይ ቡና እያልኩ በሆቴሉ የመዋኛ ቦታ ዙሪያ እንደትል የሚርመሰመሱ ህጻናትና አዋቂ ሰዎችን እመለከታለሁ:: በሰዎች ብዛትና በመዋኛ ቦታው ስፋት አለመመጣጠን እየተገረምኩ ሳለ ድንገት የጦር ወሬ የተሰማ ይመስል ህዝቡ ሁሉ መሯሯጥ ጀመረ:: የሆቴሉ ሥራ አሥኪያጅና ሌሎች ሠራተኞች ዋናተኞችንና ሌሎች ተስተናጋጆችን ማዋከብ ጀመሩ:: ሁሉም ሰው ሆቴሉን ባስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ይለማመጣሉም ያመናጭቃሉም::
Friday, 6 September 2013
አዲስ ዓመት አዲስ ስብእና!
ኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ልትቀበል አምስት ቀናት ይቀራታል:: 2006 ዓ.ም.:: በዚህ አዲስ ዓመት ሃገራችን ቢያንስ
ዳጎስ ያለ ለውጥ ማየት ይኖርባታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ:: ይህ ደግሞ ምትሃትን ወይም ተአምርን
አይፈልግም:: እያንዳንዳችን ድርሻችንን በሚገባ ከተወጣን ሊሳካ የሚችል ግብ ነው:: ከዚህ አኳያ በኔ እምነት ቀጥለው የተዘረዘሩትን ብንወጣ
በአዲሱ ዓመት ቢያንስ ትክክለኛውን የለውጥ ጎዳና እንይዛለን:: ይህ ታላቅ ሃገራዊ ጎዳና የሚጀምረው ከእያንዳንዳችን ቤትና ግቢ ነው:: ይህ እውነታ ተዘንግቶ ለውጥ ለማምጣት መሞከር የራስን ግቢ ሳያጸዱ ያካባቢን ንጽህና እጠብቃለሁ
ብሎ እንደማሰብ ነው::
Tuesday, 3 September 2013
የትግራይ ህዝብ ሥጋትና የህወሓት ፖለቲካ
የትግራይ ህዝብ ከኢሕአዴግ መንግስት ምን ተጠቅሟል? የትግራይ ህዝብና መንግስት ምን አይነት ግንኙነት አላቸው? እነዚህንና ተያያዥ ጥያቄዎችን በተመለከተ አብርሃ በላይ ከመቀሌ አጥጋቢ መልስ ሰጥቷል:: አብርሃ እንደመነሻ ያደረገው ከአንድ የትግራይ ተወላጅ የቀረበለትን ጥያቄ ነው:: ጥያቄውም ይህ ነው:: “ኢህኣዴግን ትቃወማለህ፣ ግን ህዝብን ለለውጥ ኣነሳስተህ ከህወሓት የባሱ ፅንፈኛ የፖለቲካ ድርጅቶች ስልጣን ቢይዙስ ??? ስትቃወም ስለዉጤቱም ማሰብ ኣለብህ። በምትፅፋቸውን ነገሮች ለአዳንድ የትግራይ ጠላቶች መጋበርያ እየሆንክ ነው።”
Friday, 23 August 2013
Ethiopian New Year New Promises
New years seem to herald new beginnings in all cultures worldwide. There is a huge sense of euphoria and at times seriousness in relation to them. Relatives, friends, neighbors, and even those who appear to be ‘distant’ express to each other best wishes. The first day of a new year seems to beg for a new start in one’s life.
Subscribe to:
Comments (Atom)
The Addis Paradox and Ethiopia’s Zombie State
Why can a state that appears stable in its capital simultaneously be losing governing capacity across much of its territory? This questi...