ሃሰን ዑመር አብደላ በሚል የብዕር ስም ጦቢያ መጽሔት ላይ ይጽፉ የነበሩ አቶ ዩሱፍ ያሲን ”አሰባሳቢ ማንነት ባንድ ሃገር ልጅነት፣የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ” በሚል ርዕስ ያዘጋጁትን መጽሐፍ ከሦስት ሳምንት በፊት የኦስሎ ነዋሪዎች ባዘጋጁት ፕሮግራም ላይ አስመርቀዋል:: በወቅቱም ከኦስሎና አካባቢዋ እንዲሁም ከሌሎች የአውሮፓ ሃገራት የመጡ ኢትዮጵያውያን በብዛት ተገኝተዋል:: ሰዓት አልበቃ እስኪል ድረስ ሞቅ ደመቅ ያሉ ውይይቶች መጽሐፉን በተመለከተ ተካሂደዋል:: ጥያቄዎችና ትችቶች ተነስተዋል:: ምስጋናዎችና አድናቆቶችም እንዲሁ:: ለተነሱ ወሳኝ መስለው ለታዩ ጉዳዮች ጸሐፊው አጠር አጠር ያሉ ግን ሞቅ ደመቅ ያሉ መልሶችንና እይታዎችን አቅርበዋል:: የጋለውን ውይይት ከተመለከቱ በኋላም መጽሐፉ ከአሁኑ ዓላማውን እየመታ እንደሆነ ተናግረዋል:: ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ውይይቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልና መግባባት ላይ እንዲደርስ አጠንክረው አሳስበዋል::
Saturday, 13 December 2014
Saturday, 29 November 2014
ምን አይነት ሰላማዊ ሰልፍ?
ለመጀመሪያ ጊዜ በሰላማዊ ሰልፍ የተሳተፍኩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ ግቢ ተማሪ እያለሁ ነበር:: በአራት ዓመት የትምህርት ቆይታዬ በርከት ያሉ ሰልፎች ተካሂደዋል:: አንዳንዴ የምግብ ጥራት ማሽቆልቆሉን በመቃወም ሌላ ጊዜ ነጻነትን ፍትህንና ዴሞክራሲን እንዲሁም የመሬት ክፍፍልን በመቃወም:: ምግብን በተመለከተ የተቀናጁ ሰልፎች አጀማመራቸው ምግብ-ነክ ይሁን እንጅ መደምደሚያቸው ፖለቲካ ነበር:: ድንገት ከሰልፉ መካከል አንዱ ተነስቶ "ፍትህና መብት ይከበር" ካለ ተሜ ወዲያው ተቀብሎ ያስተጋባዋል:: አንዳንዶች ደግሞ በራሳቸው ተነሳሽነት ቀድሞ የተዘጋጀ የጽሁፍ መፈክር ብቅ ያደርጋሉ:: በአቅራቢያቸው ያለ ተሜ እያነበበ ያስተጋባዋል:: ሌላው ይቀበለዋል:: የአንገት ስር እስኪወደር ድረስ ይፎከራል:: ስሜት እየጋለ ይሄዳል:: የተሰላፊው ቁጥር የሚጨምረው ሰልፉ ከተጀመረ ከበርካታ ደቂቃዎች በኋላ ነው:: መጀመሪያ ላይ ፈራ ተባ እያሉ ከዳር ሆነው የሚመለከቱ ይበዛሉ.: በኋላ ድንገት ሰልፉን የሚቀላቀሉ ይበዛሉ::
Friday, 17 October 2014
ፓትርያርክ ብፁዕ አባ ማትያስና ተግዳሮቶቻቸው
ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከተሾሙ እነሆ ሁለት ዓመት ሊሞላቸው አራት ወራት ገደማ ይቀራቸዋል:: ቅድመና ድኅረ ሹመታቸውን ተከትሎ የውይይትና የክርክር መድረኮች በኢትዮጵያም በውጭውም ዓለም ተከፍተው ነበር:: የአምስተኛው ፓትርያርክ የብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ድንገተኛ ሞት አንዳች ለውጥ ለቤተ ክርስቲያኗ ያመጣ ይሆናል ብለው የገመቱና የተመኙ ብዙዎች ነበሩ:: ሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ ሊያወርዱ እንደሚችሉ ተተነተነ:: ዳሩ ግን የእርቁ ሂደት ሳያልቅ ምርጫ ተደረገና ብፁዕ አቡነ ማትያስ በወሳኝ ድምጽ እንዳሸነፉ ተነገረ:: በዚህም የመንግስት ጫናና ማስፈራራት እንደነበረበት ተወሳ:: እርሳቸውም ነጭ ልብስ እንደማይለብሱና የቅንጦት ኑሮ እንደሚጸየፉ: ቤተ ክርስቲያን ያጣችውን ክብርና ተሰሚነት እንደሚመልሱ ተናገሩ:: «ይህን ማን አየው» በሚል ተስፋ አዲሱ ፓትርያርክ የለውጥ ሐዋርያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ቅር እያላቸውም ቢሆን የገመቱ ነበሩ::
Wednesday, 10 September 2014
አዲሱ ዓመትና ተፈላጊው ኢትዮጵያዊነት
ኢትዮጵያ ካሏት ብርቅዬ እሴቶች ውስጥ የዘመን አቆጣጠር ሥርዓቷና ተያይዘው የሚከናወኑት ተግባራት ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው:: አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓላማና ተስፋ በመሰነቅ በደመቀ ሁኔታ ያከብሩታል:: የተሻለ ለመስራት ቃል ይገባሉ:: ከአጉል ልምዶችና ከጎጅ ስብዕና ለመላቀቅ እቅድ ይነድፋሉ:: ዳሩ ግን ብዙውን ጊዜ እቅዶች የግል ህይወትን ማለትም ሥራን: ትዳርን: ቤተሰብን: ትምህርትንና ጤናን የተመለከቱ ናቸው:: ሰብአዊ: ህገ መንግስታዊና ተፈጥሮአዊ መብቶቻቸው ሲጣሱ ከማየትና በር ዘግቶ ከማማት በስተቀር በእቅድ ይዘው ለውጥ ለማምጣት ሲጥሩ የሚታዩ እምብዛም ናቸው:: በአዲስ ዓመት ራሳችንን ከማንኛውም አላስፈላጊ ጫና ነጻ ለማውጣት ስናቅድ አንታይም:: ይህም አምባና ብሄር ገነንነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የራሱን ድርሻ እያደረገ ነው::
Thursday, 7 August 2014
ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ለኢትዮጵያ: ጥናታዊ ጽሁፍ
በአገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ብሄር ገነን ሥርዓት በእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመተካት ኢትዮጵያውያን
(የሌላ አገር ዜግነት ያላቸውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንንም ማለቴ ነው) የተለያዩ መንገዶችንና ዘዴዎችን በመጠቀም
እየታገሉ ይገኛሉ:: በአገር ቤት ያሉ ወደ 100 የሚጠጉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በይፋ ሰላማዊ የትግል ስልት ይከተላሉ
ቀላል የማይባል ህዝብም በሰላማዊ መንገድ መታገል እንደሚበጅ ያምናል:: በጣት የሚቆጠሩ ድርጅቶች ደግሞ
እሾህን በእሾህ እንዲሉ መሳርያ አንስተው ወደበረሃ ገብተዋል:: እንደ ግንቦት 7 ያሉት ደግሞ ሁሉንም አይነት የትግል ስልት መጠቀም አዋጭ እንደሆነ ያምናሉ::
Wednesday, 6 August 2014
ሰላማዊ ሕዝባዊ ትግል!
ሰላማዊ ትግልን አልፎ አልፎ በሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍና በየአምስት ዓመቱ በሚመጣ ምርጫ መሳተፍ የምንወስነው ከሆነ ይህ የትግል ስልት ውጤት የለውም:: ዳሩ ግን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች እንደሚነግሩን ሰላማዊ ትግል እጅግ ሰፊ ግን ተደጋጋፊ ስልቶችን ያካትታል:: ይህ ከግምት ውስጥ ሲገባ ወደ አንድ ድምዳሜ ይወስደናል:: ሰላማዊ ህዝባዊ ትግል በኢትዮጵያ አንዱዓለም አራጌ እንደገለጸው ገና ያልተሄደበት መንገድ ነው:: እስካሁን ፖለቲካዊ ለውጥ ያልመጣው አማራጭ የሰላማዊ ትግል ስልቶች ተቀነባብረውና በቀጣይነት ሥራ ላይ ስላልዋሉ ነው::
Saturday, 12 July 2014
አገራዊ ስሜት ለምን ይጎድለናል? የመጨረሻ ክፍል
አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ቀዝቃዛ ስሜት እንዳለውና በቂ ተሳትፎ እንደማያደርግ በመደምደም የችግሩን መንስኤዎች ወይም ምክንያቶች በተከታታይ ጽሁፎች ማቅረብ ጀምሬአለሁ:: ክፍል አንድ አገራዊ ስሚት ምን ማለት እንደሆነ ካብራራ በኋላ ብዙው ኢትዮጵያዊ በብሄራዊ ጉዳዮች የመሳተፍ ዝንባሌና ፍላጎት እንዲሁም ሥነ-ልቡናዊ አቅም እንደሌለው አትቷል:: ክፍል ሁለት ደግሞ ባህላዊ አስተምህሮቶቻችን ፖለቲካዊ አገራዊ ጉዳዮችን በንቃት እንዳንከታተል ተጽዕኖ እንዳደረጉብን አብራርቷል:: እንዲሁም ብዙ ሰዎች ተሳትፎ ቢያደርጉ መንግስት በህይወታቸው: በቤተሰባቸውና በሥራቸው ላይ መከራ እንደሚያመጣባቸው በማመን "ዝምታ ወርቅ ነው"ን እያዜሙ እንደሚኖሩ አትቷል:: በዚህ የመጨረሻ ክፍል ደግሞ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች የበኩላችንን አስተዋጽዖ እንዳናደርግ ያደረጉንን ሌሎች እንቅፋቶች ለመዘርዘር እሞክራለሁ::
Subscribe to:
Posts (Atom)
The Addis Paradox and Ethiopia’s Zombie State
Why can a state that appears stable in its capital simultaneously be losing governing capacity across much of its territory? This questi...