Wednesday, 10 September 2014

አዲሱ ዓመትና ተፈላጊው ኢትዮጵያዊነት

ኢትዮጵያ ካሏት ብርቅዬ እሴቶች ውስጥ የዘመን አቆጣጠር ሥርዓቷና ተያይዘው የሚከናወኑት ተግባራት ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው:: አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓላማና ተስፋ በመሰነቅ በደመቀ ሁኔታ ያከብሩታል:: የተሻለ ለመስራት ቃል ይገባሉ:: ከአጉል ልምዶችና ከጎጅ ስብዕና ለመላቀቅ እቅድ ይነድፋሉ:: ዳሩ ግን ብዙውን ጊዜ እቅዶች የግል ህይወትን ማለትም ሥራን: ትዳርን: ቤተሰብን: ትምህርትንና ጤናን የተመለከቱ ናቸው:: ሰብአዊ: ህገ መንግስታዊና ተፈጥሮአዊ መብቶቻቸው ሲጣሱ ከማየትና በር ዘግቶ ከማማት በስተቀር በእቅድ ይዘው ለውጥ ለማምጣት ሲጥሩ የሚታዩ እምብዛም ናቸው:: በአዲስ ዓመት ራሳችንን ከማንኛውም አላስፈላጊ ጫና ነጻ ለማውጣት ስናቅድ አንታይም:: ይህም አምባና ብሄር ገነንነት ተጠናክሮ  እንዲቀጥል የራሱን ድርሻ እያደረገ ነው::


በመሆኑም አለት በውኃ ጠብታዎች እንደሚፈረካከስ በ2007 ዓ/ም ራሳችንን ከጭቆና ነጻ በማውጣት የምንወዳትን ኢትዮጵያን ነጻ እናውጣት:: ዜጎቿ የፈለጉትን ተናግረውና ሰርተው በእኩልነት የሚኖሩባት ምድር እናድርጋት:: በአዲሱ ዓመት ራሳችንን ሃገራችን ከምትገኝበትና መገኘት ካለባት ደረጃ አንጻር እንገምግም::


Pic by Laura

ቀጥለው የተዘረዘሩትን ብናደርግ በ2007 አመርቂ ውጤት ለማምጣት እንችላለን:: እንዲህ የማናደርግ ከሆነ 2007 ከ2006 ቢብስ እንጅ አይሻልም:: ብሄራዊ ለውጥ ግለሰቦች በሚያደርጉት ፍልሚያ እንደሚመጣ እንመን:: ሁሉም ሰው ራሱን ነጻ ካወጣ አምባ ገነንነት ሃገር አይኖረውም::  
 • እያንዳንዳችን በፍጹም ነጻነት እንደተፈጠርን መገንዘብና እለት እለት ከቤተሰብ: ከጓደኛ: ከጎረቤት: ከሰፈር: ከሥራ ባልደረባ: እንዲሁም ከሃይማኖት ተቋማት ማንኛውም አይነት አሉታዊ ተጽእኖ ራሳችንን መጠበቅ
 • የማንንም ነጻነት ላለመንካት መጠንቀቅ
 • በማንኛውም ሁኔታ ያላግባብ የተገፋ የተበደለ ካለ ስለሱ መጮህ መመስከር
 • ምንም ይሁን ምን እውነትን መናገርና ሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ ማበረታታት
 • የተሳሳቱ ካሉ በጥበብ ስህተታቸውን ቁልጭ አርጎ መናገር
 • የሚያድግ ድርጅት ነው የሚያድግ ፓርቲ ነው እያሉ ስተት ሲሰራ ዝም ብሎ አለማየት
 • ዘርን መሰረት ያደረገ ማህበር ፓርቲ ከመመስረት መቆጠብ
 • እኔ ፖለቲካ አያገባኝም አልችልምም ከሚል ገዳይ ቫይረስ ራስን መጠበቅ
 • በሰዎች ወይም በድርጅቶች ወይም በፓርቲዎች ድካምና ውድቀት ከመሳለቅ ችግሮች እንዲፈቱ የሚቻለውን ማድረግ
 • ለዘለቄታዊ ሰላምና እድገት ሲባል ፖለቲካዊ ትግላችን ጨቋኞችን ሳይቀር አርነት የሚያወጣ መሆን አለበት
 • ከክፉ ሥራቸው መመለስ የማይፈልጉትን ሰዎች መገሰጽ እንዲሁም ማግለል
 • ሰላዮችና መሃል ላይ ሰፍረው ወሬ የሚያቀባብሉት እንዲታረሙ መንገር
 • የማይመለሱ ከሆነ ክፉ ሥራዎቻቸውን በቃልም ሆነ በጽሁፍ ማጋለጥ
 • ለመብታቸውና ለኢትዮጵያ ሲሉ በመታገል ላይ ሳሉ የታሰሩ የተሰደዱ የተገደሉ ሰዎችን ሥራዎች ማወደስና ማሰራጨት
 • ሰውን በጻፈው እንጅ በግል ህይዎቱ ባደረገው አንተቸው
 • ጽሁፎቻችን መፍትሄ ተኮር ቢሆኑ የተወደደና ተፈላጊ ነው
 • ማህበራዊ ድር ገጾች ፎቶ ለመለጠፍ ብቻ ሳይሆን ስለሃገራችን ጉዳዮችም የምንወያይባቸው መድረኮች ይሁኑ
 • አሰቃቂ ከሆነ ስግብግብነት እራሳችንን እንጠብቅ
 • ለዘላቂ ሰላምና ለእውነተኛ ለውጥ የሚታትሩ ሰዎችን ድርጅቶችን በተቻለ ሁሉ እናበረታታ
 • ሁሉን አቀፍ የኢትዮጵያውያን ህብረቶችን በውጭ ሃገራት እንመስርት
 • ሁሉን አቀፍ ውይይትና ክርክር ከዚያም መግባባትና እርቅ እንዲመጣ እንጣር 

በ2007 ዓ/ም ራስዎንና ቤተሰብዎን ከማንኛውም አይነት ተጽእኖ ነጻ ያውጡ!!!

5 comments:

 1. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 2. ዶ/ር ተክሉ
  ለመልካም ምኞትህ አስተማሪና ጠንካራ ለሆነዉ መልዕክትህ ከልብ አመሰግናለሁ። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አንባገነኖች በወገኑ ላይ የሚደርሱት የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት በራሱ ላይ እንደደረሰ በመቁጠር በባለቤትነት ስሜት ጥቃቱን በግልና በጋራ ለመከላከል ጥረት ቢያደርግ አምባገነኖች በሃገራችን ቦታ አይኖራቸዉም። አንባገነኖች ጥቃት እንዲያደርሱብን ምክንያቶቹ እኛዉ ስለሆንን እያንዳንዱ የየራሱን ነፃነት ለማስከበር ቢጥር አምባገነኖች ዕድሜ ባልኖራቸዉም።
  ስለዚህ በሀገራችንና በሕዝቧ ላይ ወያኔ እያደረሰ ያለዉን ግፍና መከራ እያንዳንዱ ትግሉ የሚጠይቀዉን መስዋዕትነት ለነፃነታችን ትንሿን በአቅማችን አስተዋጽኦ ብናደርግ የአንባገነኖች ጥቃት በጋራ ተከላክለን ነፃነታችንን በትንሽ መስዋእትነት በአጭር ጊዜ ማግኘት በቻልን ነበር። ድር ቢያብር አንበሳ ያስር አይደል ብሂሉ!!
  መልካም አዲስ ዓመት ከነሙሉ ጤንነታችሁ ለአንተና ለቤተሰብህ እመኛለሁ።
  ዳንኤል አበበ

  ReplyDelete
 3. እያንዳንዳችን በፍጹም ነጻነት እንደተፈጠርን መገንዘብና እለት እለት ከቤተሰብ: ከጓደኛ: ከጎረቤት: ከሰፈር: ከሥራ ባልደረባ: እንዲሁም ከሃይማኖት ተቋማት ማንኛውም አይነት አሉታዊ ተጽእኖ ራሳችንን መጠበቅ!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 4. ለአዲሱ ዓመት ትምህርታዊ መልዕክትህ እናመሰግናለን ተክሉ!
  አንተንም እንኳን ለ2007 ዓ.ም. አደረሰህ!! እንደዚህ አይነት ጠቃሚ ምክሮችን ወደፊትም እንደምታበረክትልን ተስፋ አለኝ። ልብ ለሚል ሰው ምክሮቹን ስራ ላይ ካዋላቸው ለግልም ሆነ ለህብረተሰቡ ይጠቅማሉ። //ፋተ

  ReplyDelete
 5. አመሰግናለሁ ወንድም ተክሉ! በበኩሌ ቤተሰቤን በጭቆና ላለማስተዳደርና የራሴንም መብት ለመጠበቅ ከበፊቱ ይልቅ በዚህ ዓመት የበለጠ እጥራለሁ!!!

  ReplyDelete

የሁለቱ ሲኖዶሶች ፈተና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕወሓት - መሩ መንግስት ከመጣ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመጋፈጥ ላይ ትገኛለች። ኦርቶዶክስንና አማራን በተለየ መልኩ ለማዳከም ከተቻለም ለማጥፋት የትግሉ ዓላማ አድርጎ...