Saturday 24 November 2018

ብሔራዊ መግባባትና እርቅ ለኢትዮጵያ: ጥናታዊ ጽሑፍ


ሰሞኑን እንደሰማነው ከሆነ ብሔራዊ መግባባትንና እርቅን ሊያስተባብር የሚችል አካል እንዲቋቋም የሚያስችል ረቂቅ ሰነድ ለፓርላማ ተመርቷል:: ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ዋና ዋና ወንጀሎችን ለሕግ እያቀረቡ ሌላውን ተቆጥሮ ተዘርዝሮ የማያልቀውን በደልና ግፍ ግን በእርቅ መጨረስ እንደሚያስፈልግ እንደሚሻልም ጠቁመዋል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ እጅግ ሃይማኖተኛ ስለሆነና የዳበሩ የእርቅ ባህሎች ባለቤትም ስለሆነ እርቅ ብዙ ላይከብደው ይችል ይሆናል:: በግለሰብ ደረጃ  ነፍስ የተጠፋፉ ሰዎች እንኳን ከልብ ይቅር ይባባላሉ::  ውድ የቤተሰባቸውን አባል ከገደለው ሰው ጋር አብረው ለመኖር የሚያስችል አስገራሚ ልብ ያላቸው ብዙዎች አሉ:: በመሆኑም የሚቋቋመው የእርቅ ኮሚሽን ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻችንን አሟጦ በመጠቀም መግባባትን ከዚያም እውነተኛና ዘላቂ እርቅን ማምጣት ይችላል:: ብሔራዊ እርቅ የሚበረታታና ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጉጉት የሚከታተለው የሚያስፈጽመውም ጉዳይ ቢሆን መልካም ነው::   

Thursday 22 November 2018

በማጭበርበር ያልተነካካ ማንም የለም!


ካይሮ በሚገኘው የአሜሪካን ዩኒቨርስቲ የተለመደ ሥራዬን ለማከናወን ወደ መማሪያ ክፍሉ እንደገባሁ «ፕሮፌሰር እንኳን ደስ አለህ!» አለች በእድሜ ጠና ያለችው ታታሪ ተማሪዬ! «ሴት ፕሬዚደንት አገኛችሁ» አለች አከታትላ ምላሼንም እንኳን ሳትጠብቅ። «በጣም አመሰግናለሁ ብዬ ሳልጨርስ ወጣ ያለ ባህርይ ያለው ተማሪዬ «ግን እኮ ቦታው ሴረሞኒያል ብቻ ነው አለ ለስለስ ባለ ድምጽ። «ቢሆንስ? ታውቃለህ? አፍሪካ ውስጥ ሁሉም ሥልጣን ሴረሞኒያል ነው። ባይሆንማ ለውጥ በታየ ነበር» አለች ሌላዋ ተማሪ የመናደድ ምልክት እያሳየች! «ግን ሴረሞኒያል ቢሆንም ብዙ መሥራት የሚቻልበት ሥልጣን ነው! ለሴቶች ሁሉ ብዙ አንድምታዎችም አሉት በማለት ዘለግ ያለ ትንተና ሰጠች መጀመሪያ ጉዳዩን ያነሳችው። 

Who will Win: Fano or the Government?

  The government's war for "disarmament" in the Amhara region has become much more   complicated than everyone’s expectation. ...