Saturday 24 November 2018

ብሔራዊ መግባባትና እርቅ ለኢትዮጵያ: ጥናታዊ ጽሑፍ


ሰሞኑን እንደሰማነው ከሆነ ብሔራዊ መግባባትንና እርቅን ሊያስተባብር የሚችል አካል እንዲቋቋም የሚያስችል ረቂቅ ሰነድ ለፓርላማ ተመርቷል:: ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ዋና ዋና ወንጀሎችን ለሕግ እያቀረቡ ሌላውን ተቆጥሮ ተዘርዝሮ የማያልቀውን በደልና ግፍ ግን በእርቅ መጨረስ እንደሚያስፈልግ እንደሚሻልም ጠቁመዋል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ እጅግ ሃይማኖተኛ ስለሆነና የዳበሩ የእርቅ ባህሎች ባለቤትም ስለሆነ እርቅ ብዙ ላይከብደው ይችል ይሆናል:: በግለሰብ ደረጃ  ነፍስ የተጠፋፉ ሰዎች እንኳን ከልብ ይቅር ይባባላሉ::  ውድ የቤተሰባቸውን አባል ከገደለው ሰው ጋር አብረው ለመኖር የሚያስችል አስገራሚ ልብ ያላቸው ብዙዎች አሉ:: በመሆኑም የሚቋቋመው የእርቅ ኮሚሽን ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻችንን አሟጦ በመጠቀም መግባባትን ከዚያም እውነተኛና ዘላቂ እርቅን ማምጣት ይችላል:: ብሔራዊ እርቅ የሚበረታታና ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጉጉት የሚከታተለው የሚያስፈጽመውም ጉዳይ ቢሆን መልካም ነው::   


ከአራት ዓመት በፊት ብሔራዊ መግባባትንና እርቅን በተመለከተ ያካሄድኳት አጭር የዳሰሳ ጥናት ነበረች::  በወቅቱ በርከት ያሉ ውይይቶችና መጣጥፎች እያተኮሩበት የመጣው ጉዳይ ነበር:: ብሔራዊ መግባባትና እርቅ ማድረግ ለአገራችን ሰላማዊና ዘለቄታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ይነገር ነበር::ብሔራዊ መግባባትና እርቅ ማድረግ ከባህላችን ጋር አብሮ ከመሄዱም በላይ እጅግ አስፈላጊና ወቅታዊም እንደሆነ የሚሞግቱ ነበሩ:: በአንጻሩ ደግሞ ብሔራዊ እርቅ ፈጽሞ የማይሠራ ከመሆኑም በላይ የሕግንና ፍትህን መርሆች የሚቃወም እንደሆነ የሚያስጠነቅቁም ነበሩ:: አንዳንዶች ደግሞ ስለብሔራዊ መግባባትና እርቅ ማውራትና መወያየት የዋህነት አላዋቂነት ሃይማኖታዊነት እንደሆነ በድፍረት ይናገሩ ነበር:: ሌሎች ደግሞ ሃሳቡ መንግስትንና ባለሥልጣናቱን ለመታደግ የታሰበ የቆረጣ ስልት እንደሆ ይጠቁሙ ነበር::

ዳሩ ግን ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ ጠቅለል ያለ የዳሰሳ ጥናት አልቀረበም ነበር:: ጉዳዩን በተመለከተ የሚደረጉት የተናጥል ውይይቶችና የተጻፉት መጣጥፎች የተሟላ ሃሳብ ለማግኘት አላስቻሉም:: እንዲያውም በጉዳዩ ላይ ምን ያህል እንደተጻፈና ምን ምን ዝርዝር ሃሳቦች እንደተነሱ አይታወቅም ነበር:: ይህም ብሔራዊ መግባባትና እርቅ በይፋ እንደ አንድ የትግል ስልት እንዳይቆጠርና በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ዳብሮ ሥራ ላይ እንዳይውል የበኩሉን ተጽእኖ ሳያሳድር አልቀረም:: ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት አካሄድኩኝ:: የጥናታዊ ጽሑፉ ዓላማ ጉዳዩን በተመለከተ የተጻፉትን መሠረት በማድረግ አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲኖርና በርዕሱ ላይ ውይይት ተጠናክሮ  እንዲቀጥል ማነሳሳት ነበር:: ጽሑፉም በተለያዩ ዌብሳይቶች ተለቅቆ ለመነብብ ችሎ ነበር::      

በወቅቱ የተካሄደው ጥናት በርካታ ጉዳዮችን ያብራራና አቅጣጫ አመላካች ነበር:: ጥናቱ አሁንም ወደፊትም የሚካሄዱ ብሔራዊ መግባባትንና እርቅን የሚመለከቱ ዝርዝር አጀንዳዎችን ለመለየት ሊያግዝ ይችላል:: የመነሻ ሃሳቦችን ለመለየት ይጠቅማል:: በመሆኑም የዛሬ አራት ዓመት የተካሄደው ጥናት ከዚህ ቀጥሎ እንዳለ ቀርቧል::    

የጥናቱ ዓላማ

የዚህ ጥናት ዋና ዋና ዓላማዎች ቀጥለው የተዘረዘሩት ናቸው:: 
1.      እስካሁን ድረስ ስለብሔራዊ (ኢትዮጵያዊመግባባትና እርቅ  በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ምን እንደተጻፈ መመርመር  
2.     ብሔራዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ በሚገባ ያልተብራሩ ሃሳቦችን ለይቶ ማውጣት
3.     ብሔራዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ ወደፊት በጽንሰ ሃሳብና በተግባር ደረጃ ምን መደረግ እንዳለበት መጠቆም


የጥናቱ ዘዴና የመረጃ ምንጮች

በእርግጥ በድረ ገጾች በፌስቡክ በፓልቶክ ክፍሎች እንዲሁም በቴሌቪዥንና በሬዲዮ ፕሮግራሞች ጉዳዩን (ብሔራዊ መግባባትና እርቅንየተመለከቱ ውይይቶች ተካሂደው ይሆናል:: ለዚህ ጥናት እነዚህን ሁሉ የመረጃ ምንጮች ማካተቱ ጊዜ ወሳጅ መሆኑ ታምኖበታል:: በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን የጥናቱን ዓላማዎች ለማሳካት በዋና ዋና ድረ ገጾች የታተሙ መጣጥፎችን መመልከት ጠቃሚና ጊዜ ቆጣቢ ሆኖ ተገኝቷል:: አንድም የተቀናጀ ጽሑፍ በድረ ገጾች ማውጣት የተለመደ ነውና:: በመሆኑም ይህ ጥናት አራት ዋና ዋና ድረ ገጾችን በመረጃ ምንጭነት ተጠቅሟል:: እነሱም ECADF Ethiomedia Ethiopian  Review እና Zehabesha ናቸው::  እነዚህ ድረ ገጾች በኢትዮጵያዊያን ዘንድ በደንብ የሚታወቁና ፖለቲካዊ ማኅበራው ባህላዊ ሃይማኖታዊ ምጣኔ ሃብታዊና ሌሎችንም ጉዳዮች ያካተቱ በርካታና ጠቃሚ ጽሁፎች የሚታተሙባቸው ናቸው:: በአጠቃላይ ሲታይ እነዚህ ድረ ገጾች ስለብሔራዊ መግባባትና እርቅ በቂ መጣጥፎችን እንደሚያትሙ ይገመታል::  

በተመረጡት አራት ድረ ገጾችም የተጻፈውን ሁሉ አንድ በአንድ መፈተሽ አሰልቺና ጊዜ ወሳጅ ከመሆኑም በላይ አላስፈላጊም ነው:: በመሆኑም የእያንዳንዱን ድረ ገጽ የመፈለጊያ ሳጥን Search box በመጠቀም በጉዳዩ ላይ የተጻፉትን መጣጥፎች በቀላሉ ማግኘት ይቻላል:: ቀጥለው የተዘረዘሩትን የአማርኛና የእንግሊዝኛ የመፈለጊያ ቃላት ወይም ቁልፎች keywords በመጠቀም አራቱም ድረ ገጾች ተፈትሸዋል::
  • National dialogue
  • National consensus
  • National reconciliation
  •  ብሄራዊ ውይይት
  •  ብሄራዊ መግባባት
  •  ብሄራዊ እርቅ

በሌሎች ድረ ገጾች ጉዳዩን በተመለከተ መጣጥፎች ታትመው ስለሚሆን Google በመጠቀም ተጨማሪ ፍለጋ ተካሂዷል:: ይህንም ለማድረግ ከላይ የተዘረዘሩትን የአማርኛና የእንግሊዝኛ  የመፈለጊያ ቃላትን ተጠቅሜአለሁ::በአጠቃላይ ሲታይ አራቱ ድረ ገጾች በርካታ በብሔራዊ መግባባትና እርቅ ላይ የተጻፉትን ይዘው ተገኝተዋል:: ዳሩ ግን በፍለጋው ያልተገኙ ጥቂት መጣጥፎች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል:: የጥናቱ ዋና ዓላማ ስንት እንደታተመ መቁጠር ሳይሆን ምን እንደተባለ መመርመር ስለሆነ ይህ ብዙም አያሳስብም:: ለአንባቢ ግልጽ መሆን ያለበት ሌላ ጉዳይ ቢኖር ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ የሚያተኩረው የድኅረ 97 ምርጫ ጊዜን ነው:: ይህ ጥናት ምርጫውን ተከትሎ የነበሩትን የእርቅ ሙከራዎች አያጠቃልልም:: ምንም እንኳን ከዚህ ውጭ የጊዜ ገደብ ባይደረግም በርዕሱ ላይ የተጻፉት ጽሑፎች ለንባብ የበቁት 2010 ጀምሮ መሆኑን ግንዛቤ ወስጃለሁ:: የጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶች ቀጥለው ቀርበዋል::


የጥናቱ ዐበይት ግኝቶች

በአጠቃላይ ሲታይ ብሔራዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ 18 ጽሁፎች 2010 እስከ 2014 ታትመዋል:: ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ 2014 ብቻ ታተሙ ናቸው:: አብዛኞቹ (142013 እና 2014 የተጻፉ ናቸው:: ሰባቱ በአማርኛ ሲጻፉ ቀሪዎቹ 11 ደግሞ በእንግሊዝኛ ተጽፈዋል:: 16 መጣጥፎች አርእስትና ሙሉ ይዘታቸው ብሔራዊ መግባባትና እርቅ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ የተጻፉት ግን በሌላ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ነው:: ቢሆንም ግን ብሔራዊ መግባባትና እርቅ ከተነሱት ዐበይት ጉዳዮች ውስጥ ይጠቀሳል:: አብዛኞቹ መጣጥፎችን ያቀረቡት ብዙውን ጊዜ በተለያዪ ሚዲያዎች የሚታወቁ ኢትዮጵያውያን ፕሮፈሰሮች ወይም ዶክተሮች ናቸው:: ሁሉም ጽሑፎች ከዚህ ጽሑፍ መጨረሻ ላይ በጸሐፍት ስም በታተሙበት ዓመት በርዕሳቸውና ጽሑፎች በታተሙባቸው ድረ ገጾች ተዘርዝረው ይገኛሉ አንባቢያን ጸሐፍትን በቀላሉ ይለዩአቸው ወይም ያውቋቸው ዘንድ ሙሉ ስማቸውን በቅንፍ ውስጥ ጠቅሻለሁ:: አንድ ጽሑፍ በተለያዩ  ድረ ገጾች ታትሞ ቢገኝም ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ ግን መጀመሪያ የተገኘበትን ድረ ገጽ ብቻይጠቅሳል::

ምንም እንኳን ሁሉም ጽሑፎች ብሔራዊ ውይይት መግባባትና እርቅ ዋና ጉዳያቸው ቢሆንም በዝርዝር ያተኮሩባቸው ጉዳዮች እንዲሁም የሰጧቸው የመፍትሄ ሃሳቦች ግን የተለያዩ ናቸው:: በአጠቃላይ ሲታይ ግን የሚከተሉት ጉዳዮች በተለያዩ ጽሑፎች ተዳሰዋል:: 
  •       የብሔራዊ እርቅ ጥቅምና አስፈላጊነት
  •      እርቅ የሚያስፈልጋቸው አካላት
  •      እርቁን ማን ማስተባበር ወይም መጀመር እንዳለበት
  •      እርቁ እንዴት ሊካሄድ እንደሚችል 
  •      ብሔራዊ እርቅና ፍትህ  እንዴት ሊታዩ እንደሚገባ

እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የተገኙት 18 መጣጥፎች ምን እንዳስቀመጡ ቀጥሎ በአጭሩ ቀርቧል:: በቅንፍ የተመለከቱት የጸሐፍት ስምና መጣጥፎች የታተሙበት ዓመታት ናቸው:: ይህ ጽሑፍ የሚያተኩረው በዋናና ጠቅላላ ሃሳቦች ዙሪያ ስለሆነ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመረዳት በአባሪ መልክ የተያያዙትን 18ቱን ጽሑፎች ማንበብ ይጠቅማል::እንደገና የማሳስበው ጉዳይ ቢኖር 18ቱም ጽሑፎች ሁሉንም ከላይ የተዘረዘሩትን ንዑስ ጉዳ እንዳላተቱ ነው::    


የብሔራዊ እርቅ አስፈላጊነትና ጥቅም

ሁሉም ጽሑፎች ብሔራዊ መግባባትና እርቅ እጅግ ተፈላጊ የሆኑ ማኅበራዊ እሴቶችን ለመመስረትና ለማጽናት ወሳኝ እንደሆነ ያስገነዝባሉ:: እንዲሁም ከሌሎች የትግል ስልቶች አግባብነትና አተገባበር ጋር ብሔራዊ እርቅን ያወዳድራሉ ያነጻጽራሉ::  አብኞቹ ጽሑፎች ብሔራዊ እርቅ የሚያስፈልገው ኢትዮጵያ ያለችበት ዘርፈ ብዙ ችግር ተባብሶ ወደ ከባድ ቀውስ እንዳትገባ ስለሚያደርግ እንደሆነ ያትታሉ:: ያሉትን ችግሮች በህዝባዊ አመጽም ሆነ በጦርነት ለመፍታት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ተያይዞ ሊመጣ የሚችለው ቀውስ በቶሎ ማቆሚያ ሊኖረው እንደማይችል የብዙ አገሮችን ተሞክሮ በማንሳት ብዙዎች ያስጠነቅቃሉ:: ለምሳሌ ያህል ጥቂት ስለብሔራዊ እርቅ ጥቅም ወይም አስፈላጊነት የተሰጡት ማሳመኛዎች ቀጥለው ቀርበዋል::     
  •       ውጥ ምርጫ ካልሆነ በጦርነት ካልተቻለ ህዝባዊ አመጽ አደጋ ካለው ብሔራዊ የእርቅ መንግስት ከመመስረት ውጭ ሌላ ምን አማራጭ የለም (መሳይ ከበደ 2013/2014)
  •      የመንግስት ባለሥልጣናት ሳይቀሩ  ስለሚፈልጉ ብሔራዊ እርቅን ለመተግበር የማይቻል አይደለም (ተጋ 2013)
  •      በቋንቋ በዘር በሃይማኖት በፖለቲካ ምክንያት ጥላቻ ያደረባቸውን አካላት ለማገናኘት ይረዳል (ዳዊት ተሾመ 2013)
  •      ብሄራዊ እርቅ በሚገባ ከተያዘና ከተጠናቀቀ አምባገነኖችን ሳይቀር ነጻ የሚያወጣ ነው ሁሉም ተሳታፊ ስለሚሆን ጦርና የጦር ወሬዎች ታሪክ እየሆኑ ይሄዳሉ ይህ መንገድ የሰው ሕይወትም ሆነ ንብረትና ሀብት አያጠፋም በመሆኑም ይህ የፖለቲካ መስመር ጭስ አልባ ሊባል ይችላል ስለሆነም በሚያስፈራ ዝምታ ውስጥ ያለውን የሰፊውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ቀልብ ሊስብ ይችላል ለመግባባትና ለእርቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ በዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ ተቀባይነት ስላለው አስፈላጊውን ድጋፍና ማበረታቻ  ማግኘት አይከብድም በመጨረሻም ይህ የትግል ስልት ቀጣይነት ያለው ሰላምና እድገት እንዲመጣ ፈር ይቀዳል (ተክሉ አባተ 2013/2014)
  •      ቀጣይነት ላለው ሰላምና ጤናማ ማኅበረሰብ ለመፍጠር መግባባትና እርቅ ማድረግ ወሳኝ ነው (ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቂ አኢጋን 2014)  


የሚታረቀው ማን ነው?

ይህን ጉዳይ በተመለከተ በቂ ትንተና አልተሰጠበትም:: ጠቅለል ያሉና ግልጽነት የጎደላቸው ሃሳቦች ግን ተቀምጠዋል::ከአብዛኞቹ ጽሑፎች ጀርባ ተቀምጠው የሚገኙት ነጥቦች እንደሚያመላክቱት ከሆነ እርቅ የሚደረገው ወይም መደረግ ያለበት በመንግስትና በሕዝቡ መካከል ነው:: መንግስት በዳይና ሕዝብ ተበዳይ ስለሆኑ የሁለቱ መወያየት መግባባትና መታረቅ ወሳኝ እንደሆነ ያብራራሉ:: እንዲሁም አንዱ ሕዝብ ወይም ብሔር ከሌላው ጋር በጥርጣሬና በመፈራራት ስለሚኖር መታረቅ እንዳለበትም የሚጠቁሙ አሉ:: በተጨማሪም መግባባትና እርቅ በግለሰቦች መካከል ያለውን ያልጠራ ስሜትም ለማከም ማገልገል እንዳለበት የጠቆሙ አሉ (አኢጋን 2014):: ከዚህ ባለፈ ግን ጉዳዩን ብትንትን አድርጎ ያስቀመጠ ጽሁፍ የለም:: 

አንዳንዶች (ለምሳሌ ያዕቆብ ኃይለማርያም 2014) ማን ከማን ተጣላና ነው እርቅ የሚያስፈልገው ብሎ መቀለድ ዋጋ እንፍል ሲያስጠነቅቁ ሌሎች (ለምሳሌ ቴዎድሮስ ኪሮስ 2014ተክሉ አባተ 2014 ) ደግሞ በደፈናው በእርቁ መሳተፍ ያለባቸው ተቃዋሚ ኃይሎችና ድምጹን ያጠፋው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንዲሁም የፖለቲካ እስረኞች መሆን እንዳለባቸው ይጠቁማሉ:: አኢጋን ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ እርቅ የሚያስፈልገው በዘር በቋንቋ በሃይማኖትና በፖለቲካ በሚለያዩ ቡድኖች መካከል ሲሆን ከዚያ ቀጥሎ ብሔራዊ እርቅ መደረግ እንዳለበት ይጠቁማል:: በአጠቃላይ ሲታይ እርቅ የሚያስፈልገው በሕዝብና በመንግስት መካከል ብቻ ሳይሆን ወረድ ብሎም በየደረጃው መከናወን እንዳለበት ጽሑፎች ጠቁመዋል:: ይሁን እንጅ መንግስትና ሕዝብ ዋናዎቹ እርቅ የሚያስፈልጋቸው አካላት እንደሆኑ ሁሉም ጽሑፎች ያመላክታሉ::      


እርቁን ማን ያስተባብረው

ብሔ እርቁን ማን ማስተባበር እንደሚገባው ግልጽ የሆኑ ሦስት ዋና ዋና አማራጮች ተቀምጠዋል:: አንድ እርቁን መጀመርና ማስተባበር ያለበት መንግስት እንደሆነ ያተቱ አሉ (ለምሳሌ ዘላለም  እሸቴ 2014መሳይ ከበደ 2013/2014 እና ገላውዲዎስ አርአያ 2010):: ፍላጎትና ዝግጁነት ካለው መንግስት ካለበት ብሔራዊ ሓላፊነትና ካለው አቅም አኳያ ይህን የማስተባበር ሥራ ቢወስድ እንደማይከብደው ይገመታል:: ሁለት እርቁን መምራት ያለባቸው  ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው የሚሉም አሉ (ለምሳሌ ዋለልኝ መኮንን 2012  ቴዎድሮስ  2014):: ይህ አማራጭ ከፖለቲካው ሜዳ በመንግስት እየተገፉ ያሉት ሓይሎች ሂደቱን እንዲመሩት ያመቻቻል:: ሦስት መንግስትና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዋና የእርቁ አካል ስለሆኑና በዳይና ተበዳይም ስለሆኑ ነጻና ገለልተኛ ኢትዮጵያውያንን ያቀፈ አስታራቂ ግብረ ኃይል የእርቁን ሂደት መምራት አለበት የሚሉም አሉ (ለምሳሌ ተክሉ አባተ 2013 2014)::

ከነዚህ አማራጮች ለየት ያሉም አሉ:: ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባዔ እንዲጠራ ያሳሰቡም አሉ (ሰሎሞን ታረከኝ 2011):: መገናኛ ብዙኅን አስተዋጽዖ ማድረግ እንደሚችሉ ቢጠቀስም ሂደቱን ማን እንደሚመራውና እንደሚጀምረው ግን ግልጽ አይደለም:: እንዲሁም ጣቱ ትውልድ ወደብሔራዊ እርቅ የሚያደርሰውን ውይይትና ምክክር በበላይነትና በባለቤትነት መምራት እንዳለበት ያሳሰቡ አሉ (ለማዬሁ  ማርያም 2012):: የተማረ ጣቱ ትውልድ የትናንቱ ትውልድ ከሚዳክርበት የግራና የቀኝ የፖለቲካ አመለካከት ነጻ ሆኖ የእርቁን ሂደት ቢመራው እጅግ እንደሚሻል ተጠቁሟል:: ይህ እንዴት መካሄድ እንዳለበትም የመነሻ ሃሳቦች ተሰጥተዋል::    


እርቅ እንዴት ይካሄድ?

ብሔ መግባብትና እርቅ እንዴት መካሄድ እንዳለበት በርከት ያሉ ትንተናዎች ተሰጥተዋል:: ብዙዎች (ለምሳሌ ተክሉአባተ 2014ዘላለም እሸቴ 2014ሰሎሞን ታረከኝ 2011ለማዬሁ ገብረ ማርያም 2012ላውዲዎስ አርአያ 2010ከእርቅ በፊት ቀጣይነት ያላቸውና ሁሉን አቀፍ ክርክሮችና ውይይቶች መካሄድ እንዳለባቸው ጠቁመዋል:: ብሔራዊ ክርክሮችና  ውይይቶች መንግስትና ተቃዎሚ ድርጅቶች በእኩልነት ተናግዱየእያንዳንዳቸውን ጠንካራና ደካማ ጎን መለየ የሚያስችሉእንዲሁም በእውነት ላይ የተመረኮዙ መሆን እንዳለባቸው ተጠቁሟል:: ሌሎች ስለእርቅ ሂደት የተዘረዘሩ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው::
  •      በውይይቶች ጊዜ እውነታን መለየትና እውቅና መስጠት (ያዬ አበበ 2014)
  •      ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ቀድሞ መለየትከዚያም የስምምነት ሰነድ መፈራረም (ገለታው ዘለቀ 2014)
  •      ችግሮችን መመርመርተጎጅዎችን መለየት (ዳዊት ተሾመ 2013)
  •      የተሰሩ ወንጀሎችን መለየትመከላከያና ንነት ተቋማት ገለልተኛ ድረግበነጻ የመናገር መብት ማስከ (ዋለልኝ መኮንን 2012)
  •      መጀመሪያ ወጣቶች -መደበኛ ውይይቶችን በአካባቢያቸው መጀመር: ንቃተ ኅሊናን የሚያዳብሩ መርሐ ግብሮችን ማዘጋጀ: ውይይቶች ግልጽነትን ዲሞክራሲያዊ አሠራርን የተከተሉ: ሰብአዊ መብቶችንና ነጻነትን ማዕከል ያደረጉ ይሁኑ:: የራስን ችሎታና አቅም መመዘን: ያሉትን ተቋማት ለዚሁ ዓላማ መጠቀምከትናንቱ ትውልድ የአዙሪት ፖለቲካ መጠንቀቅና ከስህተቱ መማር (ዓለማዬሁ ገብረ ማርያም 2013)
  •      መንግስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር እድገት አስተዋጽዖ እንደሚያደርጉ ይመን:: እነሱንም ከማሳደድና ከመፍራት ይልቅ ያቅርባቸው:: በዘር ላይ የተመሰረተውን የፌደራል አወቃቀር እንደገና ያጢነው (ገላውዲወስ አርአያ 2010)
  •      የታሰሩትን ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲና የሃይማኖት መሪዎችና አባላትን በሙሉ መፍታት፤ የጸረ-ሽብርተኛ አዋጅ መሰረዝ፤ እና የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝባዊ ድርጅቶች አባላትና መሪዎችን በሽብርተኛነት የተፈረጁትንም አጠቃሎ የያዘ አንድ ጉባዔ በአዲስ አበባ ማካሄድ (ዕቆብ ኃይለ ማርያም 2014)
  •      የብሄራዊ እርቅ መድረኮች ይዘጋጁ (ቴዎድሮስ ኪሮስ 2014)
  •      ልብ የሆነ ይቅርታ መጠየቅና ማድረግ ( 2014


እርቅና ፍትህ  

ብሔራዊ መግባባትና እርቅ በሚጀመርበት ጊዜ የፍትህ ሀገሯ ወዴት ይሆናል? ይህ ጥያቄ ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ በቂ መልስ ያገኘ አይመስልም:: 18 መጣጥፎች ውስጥ ሦስት የሚሆኑት ብቻ ይህን ጉዳይ በግልጽ አንስተዋል::በጣም  ለተበደሉ ወገኖች ፍትህ (ለምሳሌ ካሳ መስጠት) መደረግ እንዳለበት ጠቆም ያደረጉ አሉ (ያዬህ አበበ 2014 2014):: በጣም የተበደሉት ወገኖች እነማን እንደሆኑና ምን አይነት ካሳ በማን መሰጠት እንዳለበት ግን የተብራራ ነገር የለም:: ከሁሉም ጽሑፎች ገለታው ዘለቀ (2014 ገጽ 4)የጻፉት የእርቅና የፍትህ ግንኙነት እጅግ በተሻለ መልኩ እንደሚከተለው ያብራራል:: ዋናው መልእክት እርቅ በሚደረግበት ጊዜ እንደአስፈላጊነቱ ፍትህም ሥራ ላይ ሊውልበት የሚችል እድል እንዳለ ያመላክታል:: የእርቅና የፍትህ ውሳኔዎች በአንድ ላይ ተጣጥመው መሄድ እንደሚችሉ ባህላችንን በምሳሌነት እያነሳ ይተነትናል::   

በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ብሔራዊ እርቅን በኢትዮጵያ የሚያየው እንደዚህ ነው። በዚህ ጽንሰ ሃሳብ መሠረት ብሄራዊ እርቁ ሪስቶሬቲቭ ጀስቲስን መሰረት ያደረገና በሚያድግ ዴሞክራሲ ችግሮችን ሊፈታ የሚችል ስምምነት ማለት ነው። ይህ ማለት ግን ሪትሪቢዩቲቭ ጀስቲስ ቦታ የለውም ማለት ኣይደለም። በኣሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ሙስናና ከፍተኛ ወንጀል እየፈጸሙ ያሉ ሰዎች ይህንን ሀሳባችንን እያዩ እንደ ጅልነት ኣይተው ከሥልጣን እስኪወርዱ በግፋቸው እንዲቀጥሉ በር ኣይከፍትም። የብሔራዊ እርቅ ሰነዱ እንደነዚህ ኣይነት ሰዎችን በቡድን እያየ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ወደ ፍርድ ሊያመጣቸው መቻሉ ኣያጠያይቅም። እንደ ቡድን እንደ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻችንን ዝግ እያለ ሊሰራጭ በሚችል የሪዲስትሪቢዩሽን ዘዴ ተመጣጣኝ እድገት ለማምጣት መስማማት፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎን ከባህላዊ ውህደት ስምምነት ኣንጻር ኣይቶ ከብሄር ፖለቲካ ኣውጥቶ በኣንድ ብሔራዊ ማንነት ስር ለመገንባት መስማማት፣ ዋና የሃገሪቱን ቋንቋዎችን ቁጥር መጨመር ኣጠቃላይ ፈውስን ለማምጣት ይጠቅማል። ኢትዮጵያ ሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ ላይ እንድታተኩር የሚያደርጋት ለዘላቂ ሰላምና ልማት ኣንድነት የሚረዳት ሲሆን ይህ የፍትህ ኣሰጣጥ ዘዴ በኢትዮጵያ ቡድኖች ዘንድ የተባረከና የሚበረታታ ነው። የኦሮሞ ሥርዓትን ብናይ ለሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ ትልቅ ቦታ ኣለው። ይቅር ማለትን፣ በዳዩን ከመቅጣት ይልቅ ተበዳዩን መካስን ያበረታታል።ኣማራው ኣካባቢ ያለውን የሽምግልና ሥርዓት ስናይ በኣብዛኛው ሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ የሚበረታታበት ሁኔታ ኣለ። በደቡብ፣ በምስራቅ በተለይም በሶማሌ ክልል ይህ የፍትህ ሥርዓት ከፍተኛ ተጽእኖ ኣለው


የማጠቃለያ ሀሳቦች

ይህ ጥናት ብሔራዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ በርካታ ጠቅለል ያሉ ጉዳዮችን ዳሷል:: ዝርዝር ትንተናዎችን ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መጣጥፎች ማግኘት ይቻላል:: ለማጠቃለል ያህል ግን ጥቂት ነጥቦችን ማንሳት ያስፈልጋል::

አንደኛ ምንም እንኳን የተዳሰሱት 18 መጣጥፎች የብሔራዊ መግባባትና እርቅን ጠቀሜታና አስፈላጊነት ከሌሎች የትግል ስልቶች ጋር በማነጻጸርና በማወዳደር ለማቅረብ መሞከራቸው ክፉ ባይሆንም ጉዳዩን በሌላ መነጽር መመልከቱ ይበልጥ ጠቃሚ ነው:: ብሔራዊ መግባባትና እርቅ ተጀምሮ የተወሰነ አጓጊ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ሌሎችን ትግሎች ማቆም ላያስፈልግ ይችላል:: ሌሎች ትግሎች (ለምሳሌ የተቀናጀና ደረጃ በደረጃ የሚመራ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ምናልባትም መንግስት የእርቁን ጉዳይ በሚገባ እንዲያጤነው ሊያስገድዱት ይችላሉ:: በመሆኑም የእርቅን ጠቀሜታ ለማውሳት ሌሎች ትግሎችን ማኮሰስ የግድ አይጠበቅም::

ሁለተኛ የተወሰኑ ጽሑፎች ሕዝብ ለሕዝብ መታረቅ እንዳለበት አሳስበዋል:: ምንም እንኳን ሀሳቡ በራሱ ክፉ ባይሆንም ለበርካታ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ የሆነውን አካል ማለትም መንግስትን ላላ አርገን እንድንይዝ የሚጋብዝ ይመስላል :: በመጀመሪያ ደረጃ ሕዝብ ለሕዝብ ሊጣላ አይችልም:: ከበስተጀርባ ያሉ ተንኳሽ የመንግስት ፖሊሲዎችና ፕሮፓጋንዳዎች የሕዝብን ልብ ይከፍላሉ:: መንግስት ከትንኮሳው ሁሉ ታቅቦ ሕዝቦች በሰላምና በአንድነት እንዲኖሩ ቢሠራ በአጭር ጊዜ ውስጥ የነበረን መከባበርና መተሳሰብ ይመለሳል:: ስለዚህ መታረቅ ያለበት መንግስ ከሕዝብ ጋር ነው ብዬ አምናለሁ::

ሦስተኛ መንግስትም ሆነ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች እውነተኛ እርቅን ጀምረው ማስተባበር ይችላሉ ማለት ዘበት ነው:: መንግስት እንደግለሰብ ቂመኛ በቀለኛና ትምክህተኛም ነው:: ለተቃዋሚዎች ያለው ንቀትና ጥርጣሬ መጠን የለውም:: እርቅን እሱ ቢጀምር የመሸነፍና የመዋረድ ያህል ይመለከተዋል:: ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ቢሆኑ ከመንግስት ጋር ያላቸው ቅራኔ እርቅ ለመጠየቅ የሚያበቃ አይመስልም:: ሰጥቶ የመቀበልና የማሳመን ችሎታና ፍላጎት እስካሁን አላየንም:: በመሆኑም ሌላ ገለልተኛና አንጻራዊ በሆነ መልኩ ገለልተኛ ኢትዮጵያውያን የተሰባሰቡበት አካል ያስፈልጋል:: ይህን አካል የሚያቋቁመው አካልየሚቋቋምበት መስፈርትየሚኖረው ዝርዝር የሥራ ድርሻየሚጠቀማቸው ዘዴዎች ወዘተ ግን ጥርት ብለው ለውይይት ቢቀርቡ የተመረጠ ነው:: እንዲሁም ፍትሕና እርቅ ምን ያህል የሚዛመዱና የሚቃረኑ እንደሆኑ የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ በማስገባት አስቀድሞ መተንተን ያስፈልጋል::

በአጠቃላይ ይህ አስተባባሪ ኃይል ከእርቅ በፊት በእርቅ ጊዜና ከእርቅ በኋላ ሊሟሉ የሚገባቸውን ሁኔታዎች እጅግ በዝርዝር አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አቅርቦና በውይይት አዳብሮ ሊንቀሳቀስ ይገባል:: ይህ ቀላል ሥራ ስላልሆነ የሚመረጡት ሰዎች ስሜታቸውን የሚቆጣጠሩና የሞራል ብስለት ያላቸውአዋቂዎችና አስተዋዮችእንዲሁም የመግባባትና ጫናን የመቋቋም አቅም ያላቸው ሊሆን ይገባል:: ልዩ ልዩ አይነት መስዋዕትም ለመክፈል የተዘጋጁ መሆን አለባቸው:: በመሆኑም ብሔራዊ መግባባትና እርቅ በብርቱ ልፋትና መከራ የሚመጣ እንጅ እንደሚታሰበው ሰላማዊብቻ ላይሆን ይችላል::    

የመጀመሪያው ችግር የሚሆነው ይህን አስታራቂ ኃይል ማቋቋም ነው:: ማን ነው ይህን ሊያነሳሳው የሚችለው? በተለያዩ  አካላትስ ተቀባይነት ይኖረዋልፍላጎትና ለኢትዮጵያ መልካም ራእይ ያለው ማንኛውም አካል ሊጀምረው ይችላል:: ቢያንስ ቢያንስ ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ የገመገማቸውን 18ቱን በብሔራዊ መግባባትና እርቅ ላይ ያተኮሩ መጣጥፎችን ያቀረቡት ምሁራን በመመካከር ለጉዳዩ የሚሆን መሪ ሀሳብ roadmap ማዘጋጀትና ለውይይት ማቅረብ ይችላሉ::

ጥናቱን በማካሂድበት ጊዜ የታዘብኩትና ወደፊት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ግን አለ:: ሁሉም መጣጥፎች ራሳቸውን የቻሉና ሌላውን ለድጋፍም ይሁን ለትችት በፍጹም የማይጠቅሱ ናቸው:: ስለአንድ ጉዳይ በሚጽፉ ሰዎች መካከል ምንም አይነት መናበብ’ እንደሌለ አመላካች ነው:: ሁሉም የግል ሩጫውን ተያይዞታል:: ይህን አቁመን በአንድ ጉዳይ ላይ የምንጽፍ ሰዎች መናበብ ብንጀምርና የመነሻ ሀሳብ ብናቀርብ ብሔራዊ ግዴታችንን እንደመወጣት ይቆጠራል:: የያዘውን የወረወረ ፈሪ አይባልም!!!


ስለብሄራዊ እርቅ የተጻፉ ጽሑፎች

በአማርኛ የተጻፉ
በእንግሊዝኛ የተጻፉ



No comments:

Post a Comment

Who will Win: Fano or the Government?

  The government's war for "disarmament" in the Amhara region has become much more   complicated than everyone’s expectation. ...