Friday 6 September 2013

አዲስ ዓመት አዲስ ስብእና!

ኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ልትቀበል አምስት ቀናት ቀራታል:: 2006 ዓ.ም.:: በዚህ አዲስ ዓመት ሃገራችን ቢያንስ ዳጎስ ያለ ለውጥ ማየት ይኖርባታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ:: ይህ ደግሞ  ምትሃትን ወይም ተአምርን አይፈልግም:: እያንዳንዳችን ድርሻችንን በሚገባ ከተወጣን ሊሳካ የሚችል ግብ ነው:: ከዚህ አኳያ በኔ እምነት ቀጥለው የተዘረዘሩትን ብንወጣ በአዲሱ ዓመት ቢያንስ ትክክለኛውን የለውጥ ጎዳና እንይዛለን:: ይህ ታላቅ ሃገራዊ ጎዳና የሚጀምረው ከእያንዳንዳችን ቤትና ግቢ ነው:: ይህ እውነታ ተዘንግቶ ለውጥ ለማምጣት መሞከር የራስን ግቢ ሳያጸዱ ያካባቢን ንጽህና እጠብቃለሁ ብሎ  እንደማሰብ ነው::


 ለማናኛውም ቀጥለው የተዘረዘሩትን ብንፈጽም ለውጥ የማይመጣበት ምክንያት የለም:: 

                                                Pic taken from ethiopiaforums.com
  • እያንዳንዳችን በፍጹም ነጻነት እንደተፈጠርን መገንዘብና እለት እለት ከማንኛውም አሉታዊ ተጽእኖ ራሳችንን መጠበቅ
  • የማንንም ነጻነት ላለመንካት መጠንቀቅ
  • በማንኛውም ሁኔታ ያላግባብ የተገፋ የተበደለ ካለ ስለሱ መጮህ መመስከር
  • ምንም ይሁን ምን እውነትን መናገርና ሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ ማበረታታት
  • የተሳሳቱ ካሉ በጥበብ ስተታቸውን ቁልጭ አርጎ መናገር
  • የሚያድግ ድርጅት ነው የሚያድግ ፓርቲ ነው እያሉ ስተት ሲሰራ ዝም ብሎ አለማየት
  • ዘርን መሰረት ያደረገ ማህበር ፓርቲ ከመመስረት መቆጠብ
  • እኔ ፖለቲካ አያገባኝም አልችልምም ከሚል ገዳይ ቫይረስ ራስን መጠበቅ
  • በሰዎች ወይም በድርጅቶች ወይም በፓርቲዎች ድካምና ውድቀት ከመሳለቅ ችግሮች እንዲፈቱ የሚቻለውን ማድረግ
  • ለዘለቄታዊ ሰላምና እድገት ሲባል ፖለቲካዊ ትግላችን ጨቋኞችን ሳይቀር አርነት የሚያወጣ መሆን አለበት
  • ሰውን በጻፈው እንጅ በግል ህይዎቱ ባደረገው አንተቸው
  • ጽሁፎቻችን መፍትሄ ተኮር ቢሆኑ የተወደደና ተፈላጊ ነው
  • ማህበራዊ ድር ገጾች ፎቶ ለመለጠፍ ብቻ ሳይሆን ስለሃገራችን ጉዳዮችም የምንወያይባቸው መድረኮች ይሁኑ
  • አሰቃቂ ከሆነ ስግብግብነት እራሳችንን እንጠብቅ
  • ለዘላቂ ሰላምና ለእውነተኛ ለውጥ የሚታትሩ ሰዎችን ድርጅቶችን በተቻለ ሁሉ እናበረታታ
  • ሁሉን አቀፍ የኢትዮጵያውያን ህብረቶችን በውጭ ሃገራት እንመስርት
  • ሁሉን አቀፍ ውይይትና ክርክር ከዚያም መግባባትና እርቅ እንዲመጣ እንጣር 


መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልዎ!


No comments:

Post a Comment

Who will Win: Fano or the Government?

  The government's war for "disarmament" in the Amhara region has become much more   complicated than everyone’s expectation. ...