Saturday, 13 December 2014

ኢትዮጵያዊነት: አሰባሳቢ ማንነት

ሃሰን ዑመር አብደላ በሚል የብዕር ስም ጦቢያ መጽሔት ላይ ይጽፉ የነበሩ አቶ ዩሱፍ ያሲን ”አሰባሳቢ ማንነት ባንድ ሃገር ልጅነት፣የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ” በሚል ርዕስ ያዘጋጁትን መጽሐፍ ከሦስት ሳምንት በፊት የኦስሎ ነዋሪዎች ባዘጋጁት ፕሮግራም ላይ አስመርቀዋል:: በወቅቱም ከኦስሎና አካባቢዋ እንዲሁም ከሌሎች የአውሮፓ ሃገራት የመጡ ኢትዮጵያውያን በብዛት ተገኝተዋል:: ሰዓት አልበቃ እስኪል ድረስ ሞቅ ደመቅ ያሉ ውይይቶች መጽሐፉን በተመለከተ ተካሂደዋል:: ጥያቄዎችና ትችቶች ተነስተዋል:: ምስጋናዎችና አድናቆቶችም እንዲሁ:: ለተነሱ ወሳኝ መስለው ለታዩ ጉዳዮች ጸሐፊው አጠር አጠር ያሉ ግን ሞቅ ደመቅ ያሉ መልሶችንና እይታዎችን አቅርበዋል:: የጋለውን ውይይት ከተመለከቱ በኋላም መጽሐፉ ከአሁኑ ዓላማውን እየመታ እንደሆነ ተናግረዋል:: ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ውይይቱን አጠናክሮ  እንዲቀጥልና መግባባት ላይ እንዲደርስ አጠንክረው አሳስበዋል:: 

በወቅቱም መጽሐፉን በተመለከተ ትችት እንዲያቀርቡ ከተጋበዙት ውስጥ እኔ አንዱ ነበርኩ:: ያለኝን ምልከታ በፓወርፖይንት በታገዘ ገለጻ አቅርቤአለሁ:: እነሆ ያንን ትችት እዚህ ለማቅረብ ወሰንኩኝ:: መጽሐፉን ያነበቡም ሆኑ በማንበብ ላይ ያሉ እንዲሁም ለማንበብ አመቺ ሁኔታ ለሚጠብቁ ሁሉ መጽሐፉን ለመገምገም እንደ መነሻ ሊያገለግላቸው ይችል ይሆናል:: ምልከታው ቀጥሎ የቀረበው ነው::

                                                          የመጽሐፉ የሽፋን ምስል

ይዘተ ምልከታ

qከንባብ በፊት የተደረገ ፍተሻ
q የመጽሐፉ ዓላማና ጠቀሜታ
q አወቃቀሩ
q የቴክኒክና አርትዖት ሥራዎች
q የመረጃና ማስረጃ ምንጮች
q ወሳኝ ጉዳዮች
q ማጠቃለያ 
                                           

ከንባብ በፊት የተደረገ ፍተሻ

qየርዕሱ ወቅታዊነትና ሳቢነት
q አጓጊነት
q የመጽሐፉን ዋና መልዕክት ቁልጭ አርጎ ማሳየቱ
q የመጽሐፉ የሽፋን ሥዕል የሚፈጥረው ልዩ ድባብ


የመጽሐፉ ዓላማና ጠቀሜታ

qዋና ዓላማው ለሃገራዊ ውይይትና መግባባት አስተዋጽዖ ማድረግ ነው
q ለዚህ ደግሞ ያቀረበው ወሳኝ ሃሳብ በኢትዮጵያዊነት አብሮ መኖርን ነው
q አብሮ ለመኖር ደግሞ ዜግነትን ማዕከል ያደረገ ማንነትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ነው
q ሃገራችንን እያንገላታት ላለው ክፍፍልና ቁርቁስ መፍትሄ ነው ይለናል
q ዳሩ ግን ጉዞው ቀላል እንደማይሆን ያሳስባል
q ያለመሳቀቅና ይሉኝታ ሃሳቦችን በማበራየት ወደመግባባት መደረስ እንዳለበት ያትታል
qተያያዥ ዓላማው ደግሞ "ያልተኳኳሉ እውነታዎችን" መቀበል እንዳለብን ማሳሰብ ነው  

                                                  አቶ ዩሱፍ ያሲን 

የመጽሐፉ አወቃቀር

q መጽሐፉ በ13 ክፍሎች የተደራጀ ነው
q ቀዳሚ ክፍሎች ለተከታዮቹ መሠረት ይጥላሉ
q ከጽንሰ ሃሳብ ወደ ገሃዱ ዓለም ይሄዳል 
q ከዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ወደ ሃገራዊ ትንተናዎች ይገባል
q ከትናንት ታሪካችን ወደዛሬ ተግዳሮቶቻችን ያመራል 
q ካሉብን ችግሮች ነገን ወዳማከሉ መፍትሄዎች ይንደረደራል
q ከመንግስታዊ ተኮር እውነታዎች ወደግለሰብ ታሪኮችና ገጠመኞች ይገባል 

 

የቴክኒክና አርትዖት ሥራዎች

qበአጠቃላይ ሲታይ መጽሐፉ ጥሩ የቴክኒክና አርትዖት ሥራዎች ተደርገውለታል
q ግሩም የሆነ የአማርኛ አጠቃቀም ለምሳሌ
q ፍጥምጥም
q ትወልዶሽ ዘር
q ከስትኑ
q አይገሰሴዎች
q ጠገግ እና ተሐናፂና ተገንቢ
q የፊደላት ተፋልስዎች ግን ይታያሉ
q የእንግሊዝኛ ቃላት ገብተዋል ለምሳሌ
q ካልቸር 
q ኤሊት
q ኢንስቲቲዩሽን
q ሴንሴቲቪቲ እና ኦቶኖሚ


የመረጃና ማስረጃ ምንጮች

qጽንሰ ሃሳባዊ ማዕቀፎች በሚገባ ተብራርተዋል ሥራ ላይ ውለዋል
qአለም ዓቀፋዊና ንጽጽራዊ መረጃዎች ተካተዋል
q ለመካከለኛው ምስራቅና ለኢትዮጵያ መጣጥፎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል 
q በርካታ የጥናትና ምርምር ዘርፎች ያስተባብራል
q ግን የግል ገጠመኞች እንዴት እንደተመረጡና ፋይዳቸው ምን እንደሆነ ግልጽ አደለም
q "የማኅበራዊ ሳይንስ አጥኝዎች" በሚል ሃሳቦች ይቀርባሉ
q "አንድ አጥኝ" በሚል ሃሳቦች ቀርበዋል
q "እንደምናውቀው" በሚል መላምት ሃተታዎች ቀርበዋል 

እንዲሁም በወሳኝ ጉዳዮች ላይ የተሰጡት ትንተናዎች (ለምሳሌ ስለ ኦሮሞ ብሄር ስምሪትና መስፋፋት: ስለአጼ ምኒልክ
የደቡብ ኢትዮጵያ ዘመቻ ዓላማና ውጤቱ: የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ታሪክ በአክሱም ወዘተ )ተጨማሪ መረጃዎች 
ያስፈልጋቸዋል 


ወሳኝ ጉዳዮች

qየወቅቱ ወሳኝ ጉዳዮች ተተንትነዋል ለምሳሌ
q የማንነት ምንነትና አፈጣጠሩ
q የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጉዳይ
q የኢትዮጵያ አገዛዝ በዓፄዎች ዘመን
q የኦሮሞ ብሄረተኛነት ፈታኝ ተግዳሮቶች 
q ዜግነትና ነዋሪነት 
q አሰባሳቢ ማንነትና መሠረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ 
q በቀጣይነት መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች  


አከራካሪ ጉዳዮች

q ማንነት በተጋነነ ወይም ባነሰ መረጃ ላይ ሊመረኮዝ አይችልምን?
q እንዴት መሠረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ይምጣ?
q ያለው መንግስት እንዴት ይወገድ ወይም ወደ ውይይት እንዴት ይምጣ? ገጽ 383
q አዲስ ህገ መንግስት ምን ይምሰል እንዴት ይቀረጽ? ገጽ 379
q የዜግነታዊ መንግስት ምስረታ ቅድመ ሁኔታዎች እንዴት ይሟሉ? ገጽ 388
q አሰባሳቢ ግብረ ኃይል እንዴት ይመስረት? ገጽ 428
q ይህን ሊሰራ የሚችል እስካሁን የለም ወይ? 
q ብሄራዊ መግባቢያ ኮንፈረንስ እንዴት ይካሄዳል? ገጽ 443 


ማጠቃለያ

q ወቅታዊና ወሳኝ ብሄራዊ አጀንዳዎች ስለተካተቱ መጽሐፉ የቆመለትን ግብ በሚገባ ይመታል 
q በርካታ አወያይ አከራካሪ አጨቃጫቂ ሃሳቦችን ይዟል
q መጽሐፉ ተነቦ የሚቀመጥ ሳይሆን ድርጊትን የሚጣራ ነው ለመቃወም ወይም መፍትሄ ለመሻት 
q "ያልተኳኳሉ እውነታዎችን" ዛሬ ተቀብለን ሁሉን ወይም አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ የሚወክል ሥርዓት በውይይት መገንባት እንዳለብን ያሳስባል
q ይህም በሽግግር መንግስት ምስረታ ሊጀመር እንደሚችል ይጠቁማል
q በዜግነት መብት ላይ የተመሰረት ኢትዮጵያዊያነት ካለንበት አሳሳቢ ሁኔታዎች እንደሚያወጣን የታመነ ነው 

በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት ፍቱን ብሄራዊ መፍትሄ እንደሚሆነን
እኔም በጽኑ አምናለሁ!!!     

No comments:

Post a Comment

የሁለቱ ሲኖዶሶች ፈተና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕወሓት - መሩ መንግስት ከመጣ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመጋፈጥ ላይ ትገኛለች። ኦርቶዶክስንና አማራን በተለየ መልኩ ለማዳከም ከተቻለም ለማጥፋት የትግሉ ዓላማ አድርጎ...