Friday, 19 August 2016

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር!

ታሪካዊ የለውጥ ጎዳና ለኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በአገራችን እየተደረገ ያለው የሕዝብ ተቃውሞ አስፈላጊና አበረታች እንደሆነ ሞግቻለሁ የትግሉም ዓላማ እውነተኛና ዘላቂ ዴሞክራሲና ነጻነት ማስፈን እንደሆነም ከሕዝቡ መፈክሮች በመነሳት አትቻለሁ በተጨማሪም መንግስትና ደጋፊዎቹ ትግሉን በማካሄድ ላይ ያለው ሰፊው ሕዝብ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሃይማኖት ተቋማትና የመገናኛ ብዙኅን ይህን መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ልዩና ላቅ ያለ አስተዋጽዖ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁሜያለሁ።ዝቡ የትግሉ ባለቤትና ኦዲተር ሆኖ አሥፈጻሚ አካል ወይም ልዩ ብሄራዊ ኮሚ ረጥ እንዳለበትም ለማሳየት ሞክሬ ነበር በመጨረሻም ኮሚቴው ለምንና እንዴት መመረጥ እንዳለበት ለመነሻ ያህል ጥቂት ነጥቦችን አንስቻለ በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ይህ ለውጥ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዴት እንደሚመረጥና የትግል መርሆቹና ስልቶቹ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ዘርዘር አድርጌ አቀርባለሁ    


እስካሁን ድረስ እንደታዘብነው ከሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፍጹም ውህደት እንዲፈጥሩ መጠበቅ የሚከብድ ይመስላል ያለው ብቸኛ አማራጭ እያንዳንዱ ፓርቲ የራሱን ምንነትና ማንነት እንደያዘ የጋራ ፕሮጀክቶችን መንደፍ ነውይህም ማለት ፓርቲዎች ስማቸውንና የራሳቸውን ፕሮግራም እንደያዙ በጋራ ሊሠሯቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አብሮ መለየትና መሥራት ነው: ሁሉም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ባይቻል አብዛኛው ተገናኝቶ  መወያየትና ሁሉንም የሚወክል አስተባባሪ ግብረ ኃይል ማቋቋም ወሳኝ ነው ግብረ ኃይሉ ለውጥ እስኪመጣ ትግሉን በበላይነት ይመራል አመቺና ውጤታማ የትግል ስልቶችን ለይቶ ለሁሉም ፓርቲና ለሕዝቡ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ያደርጋል የሚመረጡት የትግል ስልቶች በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በአንድ ጊዜ ሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል ተፈጻሚነታቸውን ይከታተላል የቋንቋና የባህል ልዩነት ስላለ እያንዳንዱ ፓርቲ የራሱ አባላትና ደጋፊዎች የሚበዙበትን አካባቢ በዋናነት ሊያስተባብር ይችላል 


የሚመረጡት የትግል ስልቶች (ለምሳሌ የተቃውሞ ሰልፍ ማእቀብ ማድረግ ማግለል ወዘተበሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች አንድ ላይ መደረግ አለባቸው ይህ ከሆነ የተቃዋሚው ጎራ ይበልጥ እየተባበረ እንደሄደ ሕዝብና መንግስት ያውቃሉ አስገዳጅና አማራጭ ኃይል እንዳለም አመላካች ይሆናል በሁሉም ቦታ አንድ ላይ የሚደረጉ ትግሎች የፖሊስንና የካድሬውን ስምሪት ያሳሳዋል ይህም ሊከሰት የሚችለውን የተለመደ ግድያና ዱላ እንዲሁም አፈና በእጅጉ ይቀንሰዋል መንግስት የፍርሃት መጠኑን እንዲጨምርና ሕዝብን እንዲያዳምጥ ያስገድደው ይሆናልወሳኝ ተግባራት

ለሕዝብ ቆሜአለሁ የሚል ትክክለኛ ፓርቲ በሚከተሉት መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም ይኖረዋል ተብሎ ስለሚታሰብ አስተባባሪ ግብረ ኃይሉ በቀጣይነት የሚደረጉ ሰላማዊ ትግሎች እነዚህንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ያማከሉ እንዲሆኑ ማድረግ ይችላል በሌላ አባባል የትግሉ ዓላማ የኢትዮጵያዊያንን መብትና ነጻነት ማምጣትና ሁሉንም በአንድነት አቅፋ የምትሄድ ፍጹም ዴሞክራሲያዊት አገር መገንባት ነው ይህን ዓላማ ለማሳካት ቀጥለው የተዘረዘሩትንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ማንሳትና ለነሱም አጥጋቢ መልስ ማግኘት ወሳኝነት አለው


 • ገ መንግስቱን የሚጻረሩ ጎች መመሪያዎችና ደንቦች ይሻሩ
 • ነጻና ገለልተኛ የፍትህ ሥርዓት ይቋቋም
 • ምርጫ ቦርድ ከመንግስት ተጽእኖ ይላቀቅ
 • ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ይፈቀድ
 • መንግስታዊ አሸባሪነት ይቁም
 • ፓርቲዎች በነጻ የመሰብሰብና ሰልፍ የመውጣት መብታቸው ይጠበቅ
 • የፖለቲካ  እስረኞች ያለቅድመ ሁኔታ ይፈቱ
 • መንግስት በሃይማኖት ተቋማት የሚያደርገውን ጫና ያቁም
 • በሙስና የተጨማለቁ ባለሥልጣናት ለፍርድ ይቅረቡ
 • የመከላከያ ፖሊስና ደኅንነት መስሪያ ቤቶች ብሄራዊ ተዋጽኦ ይኑራቸው ለሕዝብም ይቁሙ
 • ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ መግባባትና እርቅ  ይደረግ
 • የሽግግር መንግስት ተመስርቶ ትክክለኛና ነጻ ምርጫ ይካሄድ ወዘተረፈ

የትግል ስልቶች

ለመነሻ ያህል ወይም ለምሳሌ ይሆን ዘንድ አስተባባሪ ግብረ ኃይሉ ቀጥለው የተዘረዘሩትን የትግል ስልቶች ደረጃ በደረጃ ሥራ ላይ ሊያውል ይችላል  • ጥርት ያለ የትግል ቅደም ተከተልና ስልት በጋራ መንደፍና ፕሮግራሙንም በተለያዩ  ቋንቋዎች አዘጋጅቶ ለሕዝብና ለፓርቲ አባላት ማሳወቅ የትግሉን መጀመር ለማብሰርና ቆራጥነት ያለው አስተባባሪ ግብረ ኃይል እንተመሰረተ ለማሳየት ሕዝብን ሳይጨምር የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች ሥራ አመራሮች ሥራ አስፈጻሚዎችና ሌሎች የፓርቲዎች የቢሮ ሠራተኞች ያሉበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ማካሄድ በሰልፉ ላይ እያንዳንዱ ፓርቲ አርማውንና በጋራ የሚዘጋጁትን መፈክሮች መያዝ
 • መንግስት በሰልፉ ወቅት የሚጠየቁትን ጥያቄዎች በተመለከተ መልስ የሚሰጥበት የተወሰነ ጊዜ ገደብ ማስቀመጥ
 • ሰልፉን በቪዲዮ ቀርጾ በማኅበራዊ ሚዲያዎች መልቀቅ በጽሑፍም ማዘጋጀትና መበተን
 • መንግስት በተሰጠው ጊዜ ውስጥ አጥጋቢ መልስ ካልሰጠ በዋና ዋና ከተሞች (ለምሳሌ በአዲስ አበባ በናዝሬት በአዋሳ በጅማ በዲላበነቀምት በደሴ በባህር ዳር በጎንደር በመቀሌበደብረ ማርቆስ በአሰላ በሐረር በድሬዳዋ በሰመራ በጋምቤላ በአሶሳ ወዘተሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ በአንድ ቀን ውስጥ ማካሄድና የሰልፉን የአቋም መግለጫ ለመንግስት በጽሑፍ መስጠት አጥጋቢ መልስ መንግስት በተወሰ ጊዜ ውስጥ እንዲሰጥ ማሳሰብ
 • መንግስት በተሰጠው ጊዜ ውስጥ አጥጋቢ መልስ ካልሰጠ በግብረ ኃይሉ አማካኝነት በጥንቃቄ በሚመረጡ ጥቂት ከገዥው ፓርቲ ጋር ግንኙነት ባላቸው ወሳኝ ተቋማት ላይ ብሄራዊ ማእቀብ መጣል ማእቀቡ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ቀድሞ መወሰንና መንግስት በዚያ ጊዜ ውስጥ መልስ እንዲሰጥ ማስገደድ
 • መንግስት በተሰጠው ጊዜ ውስጥ አጥጋቢ መልስ ካልሰጠ ህዝቡ በአስተባባሪ ግብረ ኃይሉ በዝርዝር የሚቀርቡትን ሁሉንም ንብረትነታቸው የገዥው ፓርቲ የሆኑ ድርጅቶች (ባንኮችን ጨምሮ)  ላይ ማእቀብ መጣል
 • አሁንም መንግስት ለህዝብ ጥያቄ መልስ የማይሰጥ ከሆነ በመላ ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ያመረረ ሰልፍ ማድረግ መንግስት ጥያቄዎችን እንዲመልስ ዳግም ማሳሰብ
 • አጥጋቢ ምላሽ ከመንግስት እስኪገኝ ድረስ እንደአስፈላጊነቱ ስልትን እየቀያየሩ (ለምሳሌ ካድሬዎችንና ባለሥልጣናትን ከማህበራዊ ሕይወት ማግለል መንግስት በሚጠራቸው ስብሰባዎች አለመገኘት ወይም ተገኝቶ ጆሮንና አፍን መዝጋት ተቀማጭ ገንዘብን ከባንክ ማውጣት በጭቆና ምክንያት ለታሰሩት ለተደበደቡት ለተሰደዱት ለጠፉት በህብረት ሻማ ማብራትና ሥራቸውን ለሕዝብ ማቅረብና ለውይይት ማብቃት የተቀናጀ ሥራ ማቆም አድማ ማድረግ ትግሉን በሁሉም የአገሪቱ ክፍል መቀጠል…   
 • የስለላ ሥራ በመንግስት ባለሥልጣናትና በካድሬዎች ላይ ማካሄድና መጥፎ ሥራቸውን በተለያዩ  መንገዶች ለሕዝብ ይፋ ማድረግ  
 • እውነታ ላይ የተመሰረተ የፕሮፓጋንዳ ሥራ መሥራት የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ሕዝብን በመረጃ ማንቃት
 • በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የትግሉ አካል ስለሆኑ በንቃት ማሳተፍ
 • ለመንግስት የሚላኩ ውሳኔዎችን የአቋም መግለጫዎችን እንዲሁም ሥራ ላይ ያሉ የትግል ስልቶችን ለዲፕሎማቶች ማሳወቅ
 • ይህ ሁሉ ሲደረግ የመንግስት ባለሥልጣናትና ደጋፊዎች ሕዝቡን መቀላቀል ቢፈልጉ ይቅርታ እየጠየቁ እንዲቀላቀሉ ማድረግ

ማጠቃለያ

ይህ ሁሉ ሲደረግ መንግስት ዝም ብሎ አይቀመጥምከአስተባባሪ ግብረ ኃይሉ እየቀደመ የማስታገሻና የማርከሻ እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚችል ግልጽ ነው በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ልዩነት እንዲኖር ያደርጋልየትግሉን አስተባባሪዎች ሊያስር ሊያንገላታ ሊገድልም ይችላል ዝቡንም ሊያስፈራራና ሊደበድብ ሊያስርም ይችላል ይህ ሁሉ ሊመጣ እንዳለው ቀደም ብሎ መገመትና መስዋእት ለመክፈል መዘጋጀት ያስፈልጋል ለውጥ ባጭር ጊዜም ሊመጣ ስለማይችል የተለያዩ  ስልቶችን በቀጣይነት መጠቀም ወሳኝ ነው ዝብን የማንቃትና የማረጋጋት ሥራ ግን የሁል ጊዜ ተግባር ሊሆን ይገባልየፖለቲካ ፓርቲዎች ፍጹም ውህደት እንዲመጣ ከሚጥሩ ይልቅ ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ቢጓዙ ውጤታማ ይሆናሉ እንደ ድር ቀጥነው የሚታዩት የፖለቲካ ፓርቲዎች በወሳኝ የለውጥ ሥራዎች ላይ የሚተባበሩ ከሆነ እንደ አንበሳ አይሎ የሚታየውን መንግስትንና ታጣቂ አካሉን ሁሉ ሊያሸንፉ ይችላሉ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ይባል የለ!
ማሳሰያ:- ይህ ጽሑፍ የዛሬ ሁለት ዓመት ሰላማዊ ሕዝባዊ ትግል! በሚል ርዕስ ከጻፍኩት የተወሰደ ነው ጥቂት ማሻሻያ ግን አድርጌለታለሁ! የኢትዮጵያ መንግስት የሚያካሄደውን ግፍ በመቃወም ከላይ ወደታች በቅደም ተከተል በኦስሎ በሚኒያፖሊስ በጄኔቫና በሜልበርን ከተሞች የተደረጉ ሰልፎችን የሚያሳዩ  ፎቶዎችን ደግሞ  ከማኅበራዊ መገናኛ ብዙኅን ወስጃቸዋለሁ!

No comments:

Post a Comment

የሁለቱ ሲኖዶሶች ፈተና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕወሓት - መሩ መንግስት ከመጣ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመጋፈጥ ላይ ትገኛለች። ኦርቶዶክስንና አማራን በተለየ መልኩ ለማዳከም ከተቻለም ለማጥፋት የትግሉ ዓላማ አድርጎ...