Tuesday 11 September 2018

ይናገራል ፎቶ: ኢትዮጵያ ትናንት ዛሬና ነገ


በዘመነ ኢሕአዴግ/ወያኔ ኢትዮጵያውያን ብዙ ተግዳሮቶችን ሲጋፈጡ ኖረዋል:: ባለፈው 2010 ዓ/ም ጽዋው ሞልቶ ግፍና መከራ የሚያበቃበት ምዕራፍ በሕዝብ ትግል ተከፍቷል:: /ር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመመረጣቸው በፊትና በኋላ ያለውን ክስተት ሁሉ የሚዘግቡ በርካታ መጽሐፍት ሊዘጋጁ ይችላሉ:: ይሁንና በይፋ የሚታወቁ ክስተቶችን አንስቶ መወያየት ብዙም አያስቸግርም:: ባለፈው ዓመት የተከሰቱና ወደፊትም ሊከሰቱ የሚችሉ ጥቂት አስተሳሰቦችንና ድርጊቶችን በፎቶ ወይም በሥዕል መግለጽ ይቻላል:: ይናገራል ፎቶ ይባል የለ! ለእይታ ይመች ዘንድ ሁለት የጊዜ ወሰኖችን ለይቻለሁ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጡረታ እስከወጡበት ድረስ ያለውን የመንግስት አስተሳሰብና የተፈጸሙትን ግፎች በመጀመሪያ ደረጃ በሥዕል ለማሳየት ሞክሬያለሁ:: ይህንም  ከለውጥ በፊት ብዬ ሰይሜዋለሁ:: ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ኃይለ ማርያም ጡረታ ከወጡበት ጀምሮ ያለውን ሂደት ያመላክታል:: በተለይም ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመመረጣቸው በፊት የነበረውን ጥቂት ጊዜና እስካሁንም ድረስ ያለውን ያካትታል:: ይህንም ከለውጥ በኋላ ብዬ ሰይሜዋለሁ::
  

ባጠቃላይ ሲታይ የቀረቡት ሥዕላት የመንግስትን ማንነትና ምንነት በተወሰነ ደረጃ ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ::  ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ሥዕላቱን በተመለከተ ጥቂት ነገሮችን ግን ልበል::
§  ሥዕላቱን የወሰድኳቸው ከድረ ገፆች በተለይም ከፌስቡክ ወዳጆቼ ገፆች ነው:: ለዚህም ምስጋና አቀርባለሁ!
§  ሥዕላቱ ጥልቅ የሆኑ ሀሳቦችን ያስተላልፋሉ:: በደንብ ካየናቸውም ፍልስፍናዎችም ናቸው
§  የቀረቡት ሥዕላት የመንግስትን ሙሉ ማንነትና ምንነት አያመላክቱም:: በጥቂቱ ብቻ ጨልፈው ጉዳዮችን በቀላሉ እንድናያቸው እንድንረዳ ያግዛሉ
§  አንዳንዶቹ ሥዕላት በተወሰኑ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተፈጸሙ ግፎችን ቢያመላክቱም በሌሎች አካባቢዎች አለመፈጸማቸውን አያመለክቱም
§  ሁሉም ሥዕላት የተዘጋጁት ያለፈውን ግፍና መከራ እያሰብን እንድንብሰለሰል ሳይሆን የሆነብንን እንድናስታውስና ከሱም ለመማር ነው:: ለትውልድም ለማስተላለፍ ነው   
§ ይሁንና አንዳንድ ሥዕላት ለተለያዩ ትርጓሜዎች ሊጋብዙ ይችላሉ:: እርስዎም ሀገራችን ከነበረችበትና ካለችበት ሁኔታ በመነሳት የራስዎን ትርጉም ይያዙ!  
                                    
                                                      ከለውጡ በፊት
































ከለው በኋላ    





























































                                                          
                                           መልካም አዲስ ዘመን ይሁንልዎ!

No comments:

Post a Comment

Who will Win: Fano or the Government?

  The government's war for "disarmament" in the Amhara region has become much more   complicated than everyone’s expectation. ...